የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

welqyt

የሶስቱ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ

Hits: 14

መፍትሄው በብሄራዊ መግባባት የሽግግር ሂደትን እውን ማድረግ እንጂ ለ27 ዓመት የተደረገውን መድገም አይደለም

በትላንቱ ዕለት ህወሓት-መራሹ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 17 ቀናት የወሰደ ስብሰባውን እንዳጠናቀቀ በማመልከት መግለጫ አውጥቷል። ስብሰባው ከመጠናቀቁ በፊት ትልቅና አዲስ ነገር አመላካች የሆነ ውሳኔ እንደሚያሰተላልፍ በተለያየ መልክ ሲጠቁም ቢከርምም፣ የመጨረሻው መግለጫ እንደሚያመለክተው ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካለፉት ጊዜያት የተለየ ተስፋ ሰጭ ነገር ይዞ አልመጣም።

Press here for more

Hits: 198

ለሰላምና ዴሞክራሲ መሠረቱ ብሄራዊ መግባባትና የሁሉም ባለድርሻዎች ተሳትፎ ነው

በሀገራችን በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የተፈጠሩ ሁኔታዎችን በትክክል መጠቀም ባለመቻሉ ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር አልተቻለም።  ከአንድ አምባገነን ወደሌላ አምባገነን አገዛዝ ስንሸጋገር ቆይተን እነሆ አሁን ከምንገኝበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።  በመሆኑም አምባገነንነት ሰፍኖ የሕዝባችን ስቃይና መከራ እንደቀጠለ ነው። 
 

Hits: 220

ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍለው የሚያፋጁንን ጎሰኞች በአንድነት ተነስተን “በቃችሁ” እንበላቸው!!!

አሁን ኢትዮጵያውንን የገጠመን ችግር ድንገተኛ አይደለም። ችግሩ ሰፊ፣ ከባድ፣ ለበርካታ ዓመታት በፀረ-ኢትዮጵያ ባዕዳንና አገር-በቀል የጥፋት መሣሪያዎቻቸው ጥምረት በገፍ እንድንጋተው ከተጠመቀልን መርዝ ገና ገፈቱን ነው እየቀመስን ያለነው። አንዱን ብሔረሰብ በሌላው ማስፈጀት የተጀመረውም ዛሬ አይደለም። ሕወሓት እስከዛሬ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የቻለው ኢትዮጵያውያንን በቋንቋ የሚከፋፍል ‘ሕገ-መንግሥት’ አዘጋጅቶ በግድ በሕዝቡ ላይ በመጫን፣ በዕቅድና በስልት፣ ብሔረሰቦችን በሰበብ-አስባቡ እየነጣጠለ፣ እያናቆረ፣ እያጣላ፣ እያጋደለ፣ እንደሆነ ለአንድ አፍታም ልንዘነጋው አይገባንም። ይህንን ዛሬ በስፋት እየታየ ያለውን፣ ከኢትዮጵያውያን ፍፁም የማይጠበቅ፣ በብሔረሰቦች መኻል የእርስ-በርስ መጠፋፋት ለማምጣት ሆን ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲነጣጥልና ሲሰነጣጥቅ ነው የኖረው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚቻለው ሕዝቡን እርስበርሱ ማጋጨትና ማፋጀት ሲቻል ብቻ ነውና፣ ይህን በአዕምሮ-ቢስነት በአግባቡ ተግባራዊ እያደረገ ነው የሚገኘው!!! 
 

Hits: 278

አገርን ከጥፋት ህዝብን ከፍጅት ለማዳን ዛሬውኑ በጋራ እንነሳ

በአገራችን ውሰጥ የሰፈነው ከፋፋይ ሥርዓት እነሆ ህዝባችንን እርስ በርስ የሚያጋጭና የአገሪቱንም አንድነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የጣለበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ሕዝባችን በየዕለቱ ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እየተሸጋገረ ይገኛል። የቀውሱ አድማስም በአንድ ቦታ የተወሰነ ሳይሆን በየጊዜው እየሰፋ ትላንት ሰላም ነው ይባል የነበረን ቦታ ዛሬ የቀውስ ማዕከል እያደረገው ሁሉንም የኅብረተሰባችንን ክፍል፣ ሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪ እየነካ ይገኛል።በቀላል አነጋገር አገሪቱ ከዳር አስከ ዳር በቀውስ አየተናጠች መሆኗ በገሃድ አየታየ ነው

to read more

አገርን ከጥፋት ህዝብን ከፍጅት ለማዳን ዛሬውኑ በጋራ እንነሳ

 

files/pressrelease/2017a/Shengo27sstatementOct-2017.pdf

 

Hits: 394