የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

Switch to desktop Register Login

ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሥልጣኑን በጉልበት ወስዶ፣ የሕዝቡን መብት  ገፎ፣  ያገሪቱን ሃብትና ንብረት የሚዘርፈው ቡድን ሥልጣኑና አድራጎቱ ዝንተ-ዓለማዊ  እንደማይሆን ከወደቁትና  ከተወገዱት  ተመሳሳይ  መንግሥታት  ታሪክ  ገና  አልተማረም።  ከፋፍዬ እኖራለሁ የሚለው ስልቱ እየተጋለጠ በየአቅጣጫው በሕዝብ ተቃውሞ  እየተዋከበ  ይገኛል። ወደ ታሪክ መቃብር የሚገባበት ቀን እያጠረ መጥቷል። አሁን በጎንደር ቀደም ሲል በሸዋ,በተለያዩ  ያኦሮሚያ  ክልል  አካባቢወች  በጋምቤላና  በሌሎቹም  ያገሪቱ  ክፍሎች የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ  ይህን  የሚያመላክቱና  ውድቀቱን  የሚያፋጥኑ  ተቃውሞዎች ናቸው።
የአሁኑን የሕዝብ ተቃውሞ ከሌላው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው ባዶ እጁን ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በአደባባይ የሚያደርገው ትግል አሁን እንደ ፀጥታ ኃይሎቹ በመሣሪያ የተደገፈ ትግል የሚካሄድ መሆኑ ነው። መንግሥት ተብየው ትዕቢተኛና ጎሰኛ  ቡድን  ለሌላው  ዜጋ  ብቻ ሳይሆን እወክለዋለሁ የሚለውን  የትግራይ  ሕዝብ፣  በኢትዮጵያዊነቱ  ኮርቶ  በፈለገው የአገሪቱ መሬት ሠርቶ ማደር እንዳይችል እስረኛ ከማድረጉም በላይ ባላስፈላጊ  ግጭት ውስጥ ገብቶ  ደሙን  እንዲያፈስላቸው  የጥላቻና  የሽብር  ፕሮፓጋንዳ  በመርጨት  ላይ ይገኛል። የትግራይ ተወላጅ በሚረጨው የጥላቻ ቅስቀሳ ሳይታለል በስሙና በልጆቹ  ደም ሥልጣን ላይ ያሉትን የበለጸጉ አምባገነኖች ማስወገድ ይጠበቅበታል።  ለዘመናት  ከሌሎቹ ወገኖቹ ጋር ተባብሮና ነፃነቷን አስከብሮ የኖረችውን አገር አሁንም ተባብሮ ድንበሯን እየቆረሰ ለባዕዳን የሚሰጠውን ወንጀለኛና አገር አጥፊ ቡድን በቃህ ሊለው ይገባል።  ዳር ድንበሯን ለማስከበር እምቢ ላገሬ ብሎ መነሳት፣  በወገኖቹ  ጋር  አላስፈላጊ  ግጭት  ፈጥሮ ደም ከመቃባት፣ ደም ሊያቃባው የሚጥረውን ቡድን ከሥልጣኑ ሊያስወግደው በሚችለው ሕዝባዊ  ትግል  ውስጥ  የድርሻውን  ማበርከት  ይጠበቅበታል።    በአገዛዙ  ዙሪያ  የተሰበሰቡት
 
ለውጥ ፈላጊዎችና አገር ወዳዶች ሰልፋቸውን ከሕዝቡ ጋር ቢያደርጉ ሊደርስባቸው ከሚችለው የህሊና ጸጸት ሊድኑ ይችላሉ።
የሥርዓቱ አገልጋይና ተከታይ የሆነውም ወገን አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታና  ሊከሰት የሚችለውን አደጋ አጢኖ ለችግሩ ምክንያት የሆነውን መንግሥት ተብዬ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ሊሳተፍ ይገባዋል። ምርጫውን ሊያስተካክል የግድ  ይላል፤ ከሚወድቀው አገዛዝ ጋር አብሮ መውደቅ ወይም ከሚተካው ሕዝባዊ ሥርዓት ጋር አብሮ መነሳት! ሌላ ምርጫ የለም። የመከላከያ ጦርና ፖሊስም የሕዝቡን  ድምፅ  ለማፈንና ሕዝቡን በጦር ለመምታት ከአገዛዙ የሚሰጠውን ትዕዛዝ እንዳይቀበልና ከሕዝቡ ጎን እንዲሰለፍ እናሳስባለን።
የተለያዩት የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የእርስ በርስ ንትርክን አቁመው የተቀጣጠለው ትግል በድል እንዲደመደም ተባብረው አመራር ሊሰጡት ይገባል። ትግሉ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የወልቃይት፣ የትግሬ፣ የደቡብ...ወዘተ ከመሆን አልፎ አገራዊ መልክና ዓላማ እንዲይዝ የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባቸው አውቀው በዚያ መልክ ሊንቀሳቀሱ ይገባል። በግርግር ክልሌን ይዤ የራሴን መንግሥት እመሠርታለሁ በማለት ለዚያ መታገል አገሪቱን ለበለጠ ቀውስ ይዳርጋታል። የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑት የውስጥ የውጭና ኃይሎች የመጨረሻ የመዳኛ ስልት የወታደራዊ መንግሥት ቦታውን እንዲረከብ ማድረግ ሊሆን እንደሚችል ከግብፅና ከሌሎቹ አገሮች ተመክሮ መማርና መጠንቀቅ ይገባል። ስለዚህም በቀጣይ ጨቋኝና አምባገነን ሥርዓት ሲረገጡ መኖር እንዳይከተል ቅድመ ዝግጅት ማድረግ  ያስፈልጋል።
በየአካባቢው ታምቆ የቆየው ሕዝባዊ ብሶትና  ብቅ እልም ሲል የነበረው ሕዝባዊ ትግል አሁን በጎንደር የተከፈተው የድል በር እንዳይዘጋ  ተባብሮ  መቆም  ይገባዋል።  የጎንደር ሕዝብ እያሳየ ያለው ትግልና መስዋዕትነት የሚደነቅና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎኑ ቆሞ አብሮት ሊታገል የሚገባው ነው። ስለሆነም ታጋዩ የአንድነት ኃይል ትግሉን አቀነባብሮ እንዲታገል ጥሪያችንን እናቀርባለን። በዚሁ አጋጣሚም ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ሕዝብ ከሕዝብ ጋር እንዲጋጭ ለሚፈጥረው ተንኮልና ሤራ ሰለባ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን።
 
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) አገዛዙ በጎንደር ነዋሪዎች  ላይ  የወሰደውን የኃይል እርምጃና ግድያ በጥብቅ እያወገዘ በመቀጣጠል ላይ ያለው ሕዝባዊ አመጽ ብሶት የወለደው መሆኑን ያምናል፤ ይደግፋል፤ የትግል አጋርነቱንም ይገልጻል። ትግሉ ይበልጥ ፍሬያማና የለውጥ ኃይል እንዲሆን የተያያዘ አመራርና አገር አቀፍ ዓላማ ያለው እንዲሆን ያሳስባል።
የስርአቱ ባለስልጣኖች በህዝብ ላይ የሚያካሂዱት የግፍ ተግባር አሁኑኑ እንዲያቆሙ ፣ አጥብቆ ይጠይቃል። በጎንደር ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን   ቤተሰቦች፣  ወዳጅና ዘመዶችም   የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጣል


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Published in Press
Written by
Read more...

በአንድ ከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ድንገት ሰፈራቸው በእሳት ጋይቶ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ፣ምናልባት ብንድን ብለው ወደሌላ አቅጣጫ ካለው ሰፈር ለመጠለል ሲሮጡ፣ ከዛኛውም ሰፈር እንደዚሁ እሳት ተነስቶ ኑሮ፣ ብዙ ሰዎች ወደዚህኛው ሰፈር ሲገሰግሱ መሃል ቦታ ላይ ተገናኙ። ከመካከላቸው አንዱ የእኛ ሰፈር በእሳት ጋይቶ ለመጠለል ወደ እናንተ ሰፈር እየመጣን እናንተ ደግሞ በእጥፍ ቁጥር ወደእኛ እየገሰገሳችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ የደረሰብንን ጉዳት ሰምታችሁ እሳቱን ለማጥፋት ነው ወይስ እኛን ከመንገድ ላይ ተቀብላችሁ ልታስተናግዱን ነው ይኸ ሁሉ ሰው የመጣው? ብሎ የወዲያኛውን ሰፈር ኗሪ ጠየቀ። የተጠየቀውም ሰው ግር ብሎት የእሳቱ መነሳት እንዴት ከእናንተ ጆሮ ደረሰ? ለማጥፋት ልትተባበሩን ነው የመጣችሁት? ብሎ በመገረም መልሶ ጠየቀው።
ሁሉም ግራ ተጋቡና የየራሳቸውን ሰፈር መቃጠል እያነሱ ሲጨቃጨቁ በመገረም የሚያስተውሉ አንዱ አረጋዊ ሰው፤ምነው ወገኖቼ ተደማመጡ እንጂ! ሁለታችሁም እኮ እሳት ያባረራችሁ የእሳት በደለኞች ናችሁ። እንዴት መደማመጥ ይሳናችዃል? አንዳችሁ የሌላውን መቃጠል መረዳት ተስኗችሁ የእኔ ሰፈር ነው የተቃጠለው፣ የአንተ ሰፈር ሰላምና ከእሳት ነጻ ነው፤ መባባል አመጣችሁ? አንዱ የአንዱን መቃጠል መቀበልና ማወቅ እንዴት ይሳነዋል? ሰው ወዶ ቤቱንና ሰፈሩን አይለቅም። እሁለታችሁም ሰፈር እሳት አለ፣የሁለታችሁም ቤት እየጋየ ነው።እሳት እሳት ነው። አንዱን አጥፍቶ ሌላውን አይምርም።እሳት አንዱን የሚያቃጥል ሌላውን የሚያበርድ አይደለም።በሁለታችንም ሰፈር የተነሳውን እሳት የለም ብሎ መካድ ከለኮሰው ጋር ተመሳጥሮ ጉዳትን አለማወቅና አለመቀበል ነው። እሳት ሁላችንንም እያጠፋ ቤት ንብረታችንን እያወደመ ነው። ይልቁንስ አንድ ላይ ሆነን የለኮሰውን እንፈልግና ለሕግ እናቅርብ፤ ለወደፊቱም እሳት እንዳይነሳ ማገዶ ከሚሆን እንጨት የተሻለ ቤት ለመስራትና ከአደጋው ለመገላገል መላ እንምታ በማለት በሳል አስተያየትና ምክር አቀረቡ።
እኛ ኢትዮጵያውያንና ቀደም ኢትዮጵያውያን የአሁኑ ኤርትራውያን ሕዝቦች በምንኖርበት አገር የሰፈኑት አምባገነን ስርዓቶች የሚፈጁ እሳቶች ናቸው። ሁላችንም የሚፈጽሙት ግፍና በደል ሰለባዎች ነን፡፤ሁላችንም በተመሳሳይ አምባገነንና ጸረ ዴሞክራሲያዊ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች በሆኑ፣ ተደጋጋፊ ስርዓቶች ውስጥ የምንማቅቅ፣ ለስደት የተዳረግን፣ አንድ አይነት ፍላጎት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ እምነት መልክ፣ ስም ስነልቦና ያለን ዜጎች ነን።
ሁለቱ አምባገነን ስርዓቶች በሚቆጣጠሩት መሬት ውስጥ ለሚኖረው ሕዝብ የሚያቃጥሉ እሳቶች ናቸው። የእነዚህን ስርዓቶች ክፋትና በሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን በደል መካድና እንደ በጎ አድራጊ መቁጠር፣ወይም አንዱን በማርከስ ሌላውን በማንገስ ወይም በማወደስ ፣የራስን በደል እያጎሉ የሌላውን ሕዝብ ስቃይ እንደሌለ መካድ በሰው ቁስል ላይ እንጨት እንደመክተት ይቆጠራል። ለማይረባ ጥቅም ሲሉ ሌላውን መሰል ሕዝብ አሳልፎ መስጠትና ችግሩን አለመገንዘብ በታሪክ ያስጠይቃል። ከጠላት የበሉት በሶ፣ ይወጣል ደም ጎርሶ እንደሚባለው ፣ሕዝብ ከጠላው ስርዓትና መሪ ጋር አብሮ መቆም ሲገረሰስ አብሮ መጨፍለቅ እንደሚሆን ማሰቡ ብልህነት ነው። ከአንድ ሕዝብ ከጠላው መሪና ስርዓት ጋር ከመሰለፍ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በደሉን ቢያውቁለት የተሻለና በድል ማግስት የሚያኮራ ይሆናል። ከማፈርና አንገት ከመድፋት ያድናል።
በተመሳሳይ ደረጃም ለጥቂት ጊዜአዊ ጥቅም ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህወሃት መራሹን አምባገነን ስርዓት ዴሞክራቲክ አድርጎ ማቅረብና በኤርትራ መሬት ላይ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመት በፈላጭ ቆራጭነት በስልጣን ላይ የተቀመጠውን የሻእብያ መንግሥትና መሪ ዴሞክራትና አርቆ አሳቢ፣ ለሕዝብ ተቆርቋሪ አድርጎ ማቅረብ የሚያስተዛዝብ ጉዳይ ነው።
እነዚህን የሕዝብ የመከራ ምንጭ የሆኑትን አምባገነን ስርዓቶች በህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ግፍ  መካድ፣ ብሎም ለነሱ ድጋፍ መስጠትና ያልሆኑትን ናቸው እያሉ መካብ የዓለም ሕዝብ የሚያውቀውን እውነት መካድ ማለት ነው።
ከኢትዮጵያና ከኤርትራ በየቀኑ በቀይባህርና በሜዲትራንያን ባሕር አደጋን ለመጋፈጥና ካሉበት ኑሮ የነጻነት ሞትን መርጠው የሚሰደዱትን እንደ ቅንጡ አገር ጎብኝ በመቁጠር ከአገራቸው የሚያባርራቸው ምክንያት የሆነ መንግሥትና ስርዓት የለም ብሎ ማቅረብ ነው።
በሁለቱም አምባገነኖች የሚረገጡት ሕዝቦች የጋራ ችግር አለባቸው፤ ያም የመልካም ስርዓት አለመኖርና  ቀና መሪ አለመኖር ነው። አለዚያማ እንዴት ሰው አገሩን፣ ወገኑንና ቤተሰቡን ጭምር ጥሎ ለመድረሱ ዋስትና በሌለው መንገድ ወደ ማያውቀው አገር ይሰደዳል?  ድህነት ነው ቢባልም፣ድህነቱ በምን ምክንያት ተፈጠረ ብሎ መጠየቅ ይገባል። ለዚያ ደግሞ መልሱ ከስርዓቱ ጋር የተያያዘ ሆኖ ይገኛል።
የኢትዮጵያና የአሁኗ ኤርትራ ሕዝብ አብሮ በአንድ አገር ልጅነት ለዘመናት ኖሯል፡፤ወደፊትም መልሶ ሊኖር ይችላል።በሕዝብ  የሚመረጥ፣ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ፣ሕዝብ የሚያቀራርብ ስርዓት እንዲሰፍን፣ አብሮ ለመኖር የሚያስችለውን ፍላጎት እንዲዳብር የሚሻ ዜጋ አሁን ከሕዝቡ ጎን ይቆማል እንጂ ከጨቋኝ ጋር አይሞዳሞድም። ለአምባገነኖች ድጋፍና እውቅናም ሰብሳቢም አሰባሳቢም  አይሆንም።
በሁለቱም ሕዝቦች ላይ የተጫኑትን ጨቋኝና አምባገነን አገዛዞች ለውጦ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመመስረት፣ በርግጥም የህዝብን ልዖላዊነት እውን ለማድረግ፣ በሁሉም በኩል ያሉ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች በጋራ በመቆምና በመተባበር የህዝብ ወገንተኛነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ) አመለካከት በኤርትራና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት ዜጎች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው፣በስልጣንም ላይ ያሉት አምባገነኖች እንደዚሁ።
ሁለቱም ሕዝብ በማራራቅና በማለያየት ስልጣን ላይ የተቀመጡት አምባገነኖች ዕድሜ ሲያጥር ካለፍላጎታቸው ተገደው የተለያዩት የሚቀራረቡበትና በሰላም የሚኖሩበት ዕድል ይፈጠራል ብሎ ያምናል።የሁሉንም ችግር ለመፍታት የሚያስችል ስርዓት እንዲመጣ በህብረት መታገል ተገቢ ነው ብሎ ያምናል እንጂ ለትንሽና ጊዜያዊ ጥቅም ሲል ህዝብን አሳልፎ አይሰጥም።
ህወሃትና ኢሕአዴግን የሚደግፉ ኤርትራውያንም ሆኑ ሻብያንና ኢሳያስን የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ማሰብ ከሚገባቸው ነገር ውስጥ አንዱ የህዝብ መሰረታዊ መብት መከበር ከጊዚያዊ የፖለቲካ ድግፍ ማሰባበብ ባለፈ ሁኔታ ሊታይ የሚገባው ክቡር ጉዳይ እንደሆነና በመንገዳገድ ላይ ያለው የነዚህ አምባገነኖች ስርዓት ሲወድቅ ምን ይደርስብኝ ይሆን? የእኔ ተግባር ሕዝብ ሊያራርቅ ወይም ሊያቀራረብ ይችላል ወይ?ብሎ መጠየቅና መንገዳቸውን
ማስተካከልና ማረም እንደሚኖርባቸው ነው።

በየቦታው ያሉ አምባገነኖች በህዝብ ጣምራ ትግል ይወገዳሉ!!
የአንዱ ጭቁን ሕዝብ በደል ለሌላው ጭቁን ሕዝብ በደሉ፣የአንዱ ጭቁን ሕዝብ ድልም ለሌላው ጭቁን ሕዝብ ድሉ ነው።

በአንድነት፣ለአንድነት!!!

Published in Shengo Dimts
Written by
Read more...

The Ethiopian authorities must immediately and unconditionally release a prominent opposition politician facing a possible death sentence on trumped-up terrorism charges over comments he posted on Facebook, said Amnesty International.

Yonatan Tesfaye, the spokesman of the opposition Semayawi (Blue) party, was arbitrarily arrested in December 2015 and held in lengthy pre-trial detention for comments he posted on Facebook. The government says his posts against a government plan to extend the capital’s administrative authority to the Oromia region were in pursuit of the objectives of the Oromo Liberation Front (OLF), which it considers a terrorist organization.

“The Ethiopian authorities have increasingly labelled all opposition to them as terrorism. Yonatan Tesfaye spoke up against a possible land grab in Oromia, which is not a crime and is certainly not terrorism,” said Muthoni Wanyeki, Amnesty International’s Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes.

“He and many others held under similar circumstances should be immediately and unconditionally released.”

Tesfaye was arbitrarily arrested in December 2015 and held without charge for months on end. It was not until May 4, 2016 that he was charged with “incitement, planning, preparation, conspiracy and attempt” to commit a terrorist act. The state prosecutor charged that Tesfaye’s remarks were in pursuit of the OLF’s objectives.

“Yonatan Tesfaye has no demonstrated links to the OLF. His arrest is just another example of government overreach in the application of its seriously flawed anti-terrorism law. This law is once again being used as a pretext to quash dissent,” said Wanyeki.

The Ethiopian authorities should also promptly, impartially, thoroughly and transparently investigate claims that he may have been tortured or otherwise ill-treated in detention at the Maekelawi Prison, a jail notorious for its widespread use of torture.

 

Published in human rights
Written by
Read more...

 

 

Published in Shengo Videos
Written by
Read more...

 

 

Published in Shengo Videos
Written by
Read more...

 

(Nairobi) – Ethiopian security forces have killed dozens of protesters since November 12, 2015, in Oromia regional state, according to reports from the region. The security forces should stop using excessive lethal force against protesters........ Read Full Report

Published in human rights
Written by
Read more...

    “If the dignity of the individual is upheld across Africa… Americans will be freer as well… I believe that none of us are fully free when others in the human family remain shackled by poverty or disease or oppression.” President Obama, June 30, 2013

This is true in my country of origin, Ethiopia where a single party has ruled for 25 years and intends to rule perpetually. This “Orwellian” state receives over $4 billion annually, the largest in Africa and the U.S. is the largest bilateral donor. Imagine one party winning elections every 4 years in the U.S. by barring or intimidating contestants. Imagine candidates being clubbed, jailed and or forced to flee if they protest peacefully. Imagine an election without meaningful policy debates. Imagine the notion that despite $40 billion in development aid, Ethiopia is ranked as one of the poorest and most corrupt countries on the planet; per capita income is a third of the African average. This food aid dependent country supported by the U.S. lost $10 billion in four years through illicit outflow. Imagine how many factories this would build in a poor country.

It is not the stolen money that forced this American voter to write this op-ed. It is gross violations of human rights and degradation of Ethiopians, decimation of civil society and criminalization of free expression and political contest, values Americans cherish the most. In “Journalism is not a crime” Human Rights Watch had forewarned donors “The Ethiopian government’s systematic repression of independent media has created a bleak landscape for free expression ahead of the May 2015 general elections…at least 22 journalists, bloggers and publishers were criminally charged, and more than 30 journalists fled the country.” The Ethiopian government uses the 2009 Anti-Terrorism and the Charities and Societies Organizations (CSO) legislations as blunt instruments to punish those who stand up for freedom, democracy and the rule of law. Employment opportunities are guided by ethnicity and political affiliation. Don’t you think these conditions contribute to instability and terrorism? Is this in America’s long-term interest?

Freedom House’s Freedom in the World Report 2015 ranks Ethiopia “43 out of 49 Sub-Saharan African countries” that are not free. The Committee to Protect Journalists (CPJ) identifies Ethiopia among the “two top jailers of journalists in Africa and among the top four in the world.” It is my genuine belief America’s long-term security and trade interests and the interests of the Ethiopian people will be best served by promoting and defending respect for human rights and freedoms, civil society, accountable and representative governance in Ethiopia unconditionally. At minimum, the U.S. should stop providing aid dollars to a regime that decimates independent media, obstructs the participation of opposition parties and jails or forces critics to flee in droves. These requests are consistent with America’s own core values of political pluralism, free expression and freedom of the press, respect for human rights, democracy and the rule of law. No free, fair, open and credible election would take place on May 24, 2015 under this suffocating environment. I do not believe Americans want dictatorship over democracy.

Consider an editorial comment on May 6, 2015, “Elections, Ethiopian Style” by Human Rights Watch. “Since the last election, the ruling party has exerted more control and increased its repression of basic liberties, including the rights to free expression, assembly and association…As Ethiopians go to the polls in late May, 2015, prospects for the opposition to fully and fairly campaign are grim” and a similar editorial by the Washington Post on May 1, 2015 “Make-believe in Ethiopia” rebutting remarks by the Department of State’s Undersecretary for Political Affairs, Wendy Sherman that “Ethiopia is a democracy that is moving forward in an election that we expect to be free, fair, credible, open and inclusive.” I commend the post for stating the facts. “The regime’s repression deserves condemnation, not praise, from Washington.” I fear genuinely that the Ethiopian government has created a suffocating environment of disempowerment engendering terrorism that may lead to the fracturing of an already polarized and volatile country. I urge the Government of the United States and American voters to help avert another failed state in the Horn of Africa.

Would you urge your representatives in Congress and Government of these United States to do all they can so that your taxes no longer shore up one the most oppressive governments in Africa?

Aklog Birara, Ph.D. is a retiree from the World Bank and is President of the Center for Inclusive Development. He may be reached at This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Read more...

External links are provided for reference purposes. Shengo is not responsible for the content of external Internet sites. Copyright © 2013 የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

Top Desktop version