የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

የአንድነትና የመኢአድ ስምምነት፣ ሊበረታታ የሚገባው መልካም ተግባር ነው

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ)፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)ና አንድነት ለዴሚክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በትላንትናው ዕለት ለውህደት  የሚያበቃ የመጀመሪያ ስምምነት በመፈራረማቸው የተሰማውን ታላቅ ደስታና አድናቆት ይገልጣል።

ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባትና የሰብዓዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እውን የሚሆንባት፣ በዜጎች እኩልነት ላይ የጸና መሰረት ያላት ዴሞክራሲያዊት ሀገር በጋራ ለመገንባት እንድንችል የስርዓት ለውጥን የሚሹ የተቃዋሚ ድርጅቶች  ሁሉ ጥቃቅን ልዩነቶችን ትተው በመተባበርና አንድ ላይ በመምጣት ህዝባዊ ኃይሉ በአንድነት በመቆም አምባገነናዊነትን በጽናት እንዲታገል ማብቃት ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህም አንጻር፣ ውስብስብ ችግሮችን አልፈውና የብቸኛነት ድንበርን ሰብረው በአንድነትና በጋራ ዓላማ መሰለፍን መምረጥ ትልቅ አስተዋይነትና ለወደፊት ጉዞም አስተማማኝ መሰረትን የሚጥል  በመሆኑ በሁለቱ ድርጅቶች በኩል የደረሱበት ቅድመ ውህደት ስምምነት ትልቅ ተስፋ ሰጭና  በሁሉም የአንድነትና የዴሞርራሲ ኃይላት ሊበረታታ የሚገባ ነው።  ሌሎቹም በተናጠል እየታገሉ የሚገኙ በኢትዮጵያዊነታቸውና በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ኃይሎች ይህን የመኢአድንና የአንድነትን ፈለግ እንደምሳሌ ወስደው የመተባበርንና የአንድ የመሆንን ጎዳና እንዲመርጡና   አስፈላጊውን እርምጃም ሳይዘገዩ እንዲወስዱ  በአንክሮ ለማሳሰብ እንወዳለን።

እንደዚህ ያሉ ሂደቶች እንዳይሳኩ በጸረ አንድነት ሃይሎች መሰናክሎች መዘርጋታቸው አይቀሬ ነው። ህወሓት/ኢሕአዴግ   ለሚሸርበው ተንኮልና ለሚያደርሰው ጉዳት ፣ ሳይበገሩ  ያሰቡትን ዓላማ ከግብ ማድረስ ግን  የጀግንነት ሙያ ነው።

የአንድነትና የመኢአድ አባላትና መሪዎች ለገጠማቸው ችግርና የገዥው ቡድን ተጽዕኖ ሳይንበረከኩ ወዳቀዱት የውህደት መጀመሪያ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ሊያኮራቸው የሚገባና የሚመሰገኑበት ሲሆን ወደ ዘላቂ ግብ ለመድረስም በሚያደርጉት ጉዞ የበለጠ  መሰናክልና ዕይን ያወጣ አፍራሽ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል አውቀው እስካሁን እንዳደረጉት ሁሉ  በድፍረትና በብልሀት የጀመሩትን ጉዞ በስኬት እንደሚያጠናቅቁ ታላቅ ተስፋችን ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ቀደም ሲልም ሆነ አሁንና ወደፊት በተናጠል የቆመው የአንድነትና የዴሞክራሲ ጎራ ተባብሮ በአንድ የጋራ አመራር ስር ተሰልፎ ትግሉን አቀናጅቶ እንዲቀጥል ማድረግ ከተመሰረተባቸውና እውን ለማድረግ  ከፍተኛ ጥረት ከሚያደርግባቸው ዋና ዋና ራዕዮቹ ውስጥ አንዱ ነው። ስለሆነም፣ በመኢአድና በአንድነት መካከል የተጀመረው የውህደት ሂደት ያስደሰተው ሲሆን ከፍጻሜ ደርሶ ለማየት ከፍተኛ ጉጉት አለው። ጅምሩ የተሳካ እንዲሆን ምኞቱን እየገለጸ ለቀጣዩ የትግል ጉዞ አብሮ ለመቆም ያለውን ፍላጎትና አጋርነቱን ከወዲሁ ሊገልጽ ይወዳል።

አንድነታችን  ለድላችን  ዋስትናችን ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ)

Hits: 1317

ሸንጎ በሲያትል ዋሽንግተን የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አካሄደ

ትልቁ  የኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ስበስብ የሆነው የኢትዮጵያ  ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሽንጎ) የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት የሁኑት ፕሮፊሰር አቻምየለህ ደበላና ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እሁድ ግንቦት24 ቀን2006  (ጁን1፣2014) ፣በሲያትል(አሜሪካ) ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል።

በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ሁለቱም የሽንጎው ተወካዮች  በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ፣ በሽንጎው ራዕይና እንቅሰስቃሴ እና በዜጎች ተሳትፎ ላይ ሰፊ ገለ ጻአድርገዋል። የፕሮፊሰር አቻምየለህ ደበላና የዶ/ር አክሎግ ቢራራን ገለጻ በማስከተልም ስፊ ጥያቄና መልስ እና አርኪ  ውይይት ተካሂዷል።

ሸንጎ ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባዋችን በተለያዩ ሀገሮችና ከተሞች ውስጥ በማካሄድ  በአለም ዙሪያ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለማስወገድ የሚስችል ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰቡን እንደሚቀጥል ታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሸንጎው ዲፕሎማቲክ እንቅስቃሴ በማካጠናከር ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ከፍተኛ ድጋፍን ለማስገኘት ሰፊ እንቅስቃሴ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

በስያትል የተካሄደውን ስብሰባ ላሰተባበሩ እንዲሁም በስብሰባው ላይ  ለተገኙ ሁሉ ሽንጎ ምስጋናውን አቅርቦ፣ ይህ ትብብር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጧል። በሲያትል የኢትዮጵያ ወጣቶች ስብስብ፣ እንዲሁም ሞሲሊም ወገኖቻችን በተለይ ደግሞ ነጃሽ ጀስቲስ በመባል የሚታወቀው ድርጅት አባላት ላደረጉት ትብብር ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

Hits: 1198

Ana Gomes' Letter Concerning The Recent Repression in Ethiopia

Brussels, 06 May 2014

Subject: Renewed crackdown on press freedom and political dissent in Ethiopia

Dear Madam High Representative,

Recently, Ethiopian authorities arrested six bloggers and three journalists and charged them with working with a foreign organisation to incite public  violence through social media, in one of the worst crackdowns against free expression in the country. According to Human Rights Watch, on the afternoon of April 25, police detained six members of a group known as the “Zone9” bloggers – Befekadu Hailu, Atnaf Berahane, Natnael Feleke, Mahlet Fantahun, Zelalem Kibret, and Abel Wabela

– at their offices and in the streets. Tesfalem Weldeyes, a freelance journalist, was also arrested during the operation. Edom Kassaye, a second freelance journalist, was arrested on either April 25 or 26; the circumstances of her arrest are unclear but all eight individuals were apparently taken to Maekelawi Police Station, the federal detention center in Addis Ababa, the capital.......Read the full Letter

 

Hits: 1110

እኛም ከሚሊዮኖች ውስጥ ነን

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)፣ በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እየተቀነባበረ በሚካሄደው “የሚሊዮኞች ድምፅ” ንቅናቄ ውስጥ“ኛም ከሚሊዮኞቹ ውስጥ ነን” በማለት ለተጀመረው እንቅስቃሴ ሙሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። በዚህም መሠረት የዚህ እንቅስቃሴ አካልነታችንን በተግባርለ መግለፅ በአዳማ (ናዝሬት) የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በስፖንሰርነት ለመደገፍ እድሉ ስለገጠመን እጅግ ደስተኛ ነን።...... ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

Hits: 1029

“እኛም ከሚሊዮኖቹ ውስጥ ነን”

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)፣ በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እየተቀነባበረ በሚካሄደው “የሚሊዮኞች ድምፅ” ንቅናቄ ውስጥ“ኛም ከሚሊዮኞቹ ውስጥ ነን” በማለት ለተጀመረው እንቅስቃሴ ሙሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። በዚህም መሠረት የዚህ እንቅስቃሴ አካልነታችንን በተግባርለ መግለፅ በአዳማ (ናዝሬት) የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በስፖንሰርነት ለመደገፍ እድሉ ስለገጠመን እጅግ ደስተኛ ነን።...... ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

Hits: 1039