የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የተወሰነውን እስራት ሸንጎ ያወግዛል።

ሐምሌ 29፣ 2007 (ኦገስት 5፣ 2015)

ሰኞ  ሐምሌ 27፣ 20017  (ኦገስት 3፣ 2015) በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የህወሓት/ኢህአዴግን ፍላጎት በማስፈጸም የሚታወቀው ፍርድ ቤት ከሰባት ዓመት እስከ 22 ዓመት የሚደርስ እስራት እንደበየነባቸው ይፋ ሆኗል።

የሞስሊሙ ኅብረተሰብን የተቃውሞ ድምጽ መሠረት በማድረግ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ በማፈላለግ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩት እነአቡበከር አህመድ የታሰሩት ከሁለት ዓመት በፊት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ እምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት አመራሩን ለመቆጣጠርና እሱ የሚፈልገውን የእምነት ፈርጅ ኢትዮጵያውያን  ሞሰሊሞች በግዴታ እንዲቀበሉ ያውጠነጠነውን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር እምቢ ማለታቸውን ተከትሎ እንደነበር ይታወሳል።

ሸንጎና ሌሎችም እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሀገራችን ውስጥ የሞስሊሙ ማኅበረሰብ መንግሥት በሃይማኖቱ ውስጥ እንዳይገባ ያቀረበውን ጥያቄ በማክበር እጁን እንዲያነሳ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ ቆይቷል።  ሆኖም እንደተለመደው ሁሉ ከራሱ ሌላ ማንንም ማዳመጥ ያልለመደው  የህወሓት/ኢህአዴግ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ሃላፊነት የጎደለው እርምጃ በሚቆጣጠረው ፍርድ ቤት በኩል ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል።

ይህ እርምጃ የሞስሊሙን ኅብረተሰብ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄ ይበልጥ ያጠናክረዋል እንጂ  አያዳክመውም። እንዲያውም የሞስሊሙ ህብረተሰብ አባላትና ሌሎችንም በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ጥያቄን አቅርቦ በሕግ መብትን ማስከበር አይቻልም ወደሚል መደምደሚያ እንዲደርሱና አላስፈላጊ በሆነ ጎዳና እንዲጓዙ የሚገፋፋ ነው። ይህ ለሀገራችን ሰላምና መረጋጋት የሚረዳ ሳይሆን አደጋን የሚጋብዝ እጅግ ሃላፊነት የጎደለው እርምጃ ነው።

ሸንጎው በሞስሊሙ ኅብረተሰብ በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የፖለቲካ መሳሪያ የሆነው ፍርድ ቤት የወሰደውን እርምጃ አጥብቆ ያወግዛል። የሞስሊሙ ኅብረተሰብም መሰረታዊ መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ የትግል አጋርነቱን ያረጋግጣል።

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያካሂደውን በሃይማኖት ነፃነት ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት እንዲያወግዝ  ሸንጎ  ጥሪውን ያቀርባል። የህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊዎችም አገዛዙ ከቀን ወደቀን ሀገራችንንና ሕዝባችንን ወደተባባሰ አደገኛ ጎዳና መውሰዱን እንደቀጠለ መሆኑን እንዲገነዘቡ እያሳሰበ፡ በዚህም ምክንያት ለሚከተል አለመረጋጋት ተጠያቂው ህወሓት/ኢህአዴግ እንደሆነ ሁሉም እንዲገነዘበው እናሳስባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Hits: 1025

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ሶስተኛ ጉባዔ ተከናወነ

ከሰኔ ፳፮ እስከ ፰ ፪ ሺህ ፯ ዓ. ም  (July 3rd to July 5th 2015) በዋሺንግተን ዲሲ የተካሄደው የሸንጎው ሦስተኛ ጉባዔ  በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷል። ጉባዔው ሸንጎ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያካሄዳቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችና የልዩ ልዩ የስራ ግብረ ኃይሎች ሪፖርት ገምግሞ በሚቀጥሉት ዓመታት ትኩረት ለሚያደርግባቸው ግቦች ስኬታማነት፤ የሰው፤ የገንዘብና ሌላ ቁሳቁስ፤ የመረጃ፤ የመገናኛና የሕዝብ ግንኙነት፤ የዲፕሎማሲ፤ የወጣቶችና ሴቶች ተሳፎ፤ በሃገር ቤትና በውጭ ከሚንቀሳቀሱ መሰል ድርጅቶች ጋር የግንኙነት አቅሙን ለማጠናከር... ወዘተ ከመቸውም የበለጠ ጥረት እንደሚያደርግ ወስኗል።  

አንደሚታወቀው  ሸንጎ እንዲመሰረት ያስገደደው ዋና የፖለቲካ አደረጃጀትና የአመራር ክፍተት የተበታተነውና እርስ በእርሱ የሚጠላለፈው አገር ወዳድ ተቃዋሚ ኃይል ተባብሮ፤ ተመካክሮ፤ ተናቦ፤ ተደራጅቶ፤ ብቁነት ያለው አመራር መስርቶና የጋራ ሰነድ አዘጋጅቶ በተከታታይ ትውልድና ታሪክ ሊጠቀስ የሚችል አስተዋፆ ለማድረግ ሲችል ብቻ ነው የሚል እምነት ስላለው ነው።

አሁንም እንዳለፉት ሃያ አራት አመታት የሚታየው የፖለቲካ ሁኔታ ከህወሓት/ኢህአዴግ ጥንካሬ ይልቅ የተቃዋሚው ዘርፍ መፍረክረክ፤ መከፋፈል፤ መጋጨት፤ መነታረክ፤ አለመተማመን፤ መጠላለፍ፤ ራሱን ለሰርጎ ገቦች ማጋለጥ... ወዘተ ነው። በጉባዔው ትንተናና እምነት የተቃዋሚው ኃይል አብሮና ተባብሮ ለመስራት አለመወሰን ለአፋኙ፤ በዝባዡና፤ ጠባብ ጎሰኛው አምባገነን የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት በገንዘብ ሊገዛው የማይችል አስተዋፆ እያደረገለት ነው። በመግለጫውና ሃተታው እንደምናብራራው ተሳስቦና ተቻችሎ በአንድነት ከመስራት ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም። ሰብሳቢ የሆኑ የአንድነት ኃይሎች በሙሉ የሚጋሯቸው፤ ለጋራ ሰነድ ዝግጅት ጠቃሚ ይሆናሉ ብለን የምንገምታቸው አስኳል ጉዳዮች አሉ።

ለዚህ ይጠቅማል ብለን የምንገምተው በሸንጎ ውስጥ የተጣመሩት የፖለቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶችና የታወቁ አገር ወዳድ ግለሰቦች ተስማምተውና ተጋርተው የሚመሩባቸውን አምስት መርሆዎች መገምገም ነው። እነዚህም፤  

አንድ፤ በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ በመላው ሕዝቧ የሥልጣን ባለቤትነትና ሉዑላዊነት ጽኑ ዕምነት ማስተጋባት፤

ሁለት፤ በሕግ ፊት የሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች እኩልነትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር ወሳኝ መሆናቸውን መቀበል፤  

ሶስት፤ ፍትኅ የሰፈነበትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሥርዓት መመስረት አስፈላጊ መሆኑን ማመን፤

አራት፤ በድርጅቶች ውስጥና መሃከል ዴሞክራሲያዊነትን መመሪያ አድርጎ በስራ ላይ ማዋልና፤

አምስት፤ በስልጣን ላይ የሚገኘው የህወሓት/ኢህአደግ አገዛዝ ለዴሞክራሲ መስፈን፤ ለእርጋታ፤ ለሰላም፤ ለዘላቂና ፍትሃዊ እድገት እንቅፋት የሆነ ስርዓት በመሆኑ መወገድ እንዳለበት መቀበልና ያልተቆጠበ ጥረትና አስተዋፆ ማድረግ ናቸው።

ጉባዔው፤ እነዚህን ግቦች ስኬታማ ለማድረግ የመጀመሪያዎቹ ጊዜ የማይሰጡ ትኩረቶች ኢትዮጵያን ከመፈራረስ (አገር ለማዳን) እና ሕዝቧን ከእርስ በእርስ እልቂት ለማዳን በአንድነት መነሳት ነው የሚል ነው። ኢትዮጵያ ከጠፋች ሌላው ትግል ትርጉም የለውም ከሚል ስምምነት ላይ ደርሰናል።

ጉባዔው እነዚህ መርሆዎች አሁንም አግባብ እንዳላቸው ተቀብሎ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ በጥናቶች የተደገፈ ጥልቀትና ስፋት ያለው ሰፊ ውይይት አድርጓል። ከእነዚህ መካከል ትኩረት የሰጣቸው አስኳል ጉዳዮች የግንቦቱ የይስሙላ “ምርጫ” ትርጉመቢስነት፤ የገዢው ፓርቲና የተቃዋሚው ጎራ ጠንካራና ደካማ ጎኖች፤ አገር ቤትና ውጭ ከሚገኙ የአንድነት ዘርፍ የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ ሰፊና ጠንካራ የሆነ ግንባር መስርቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አግባብ ያለው አማራጭና የጋራ ሰነድ በማዘጋጀት፤ ወጣቶችና ሴቶች በሰፊው የሚሳተፉበትን ሁኔታ በማመቻቸት፤ በብሄር/ብሄረሰብና በየክልሉ ስም ተደራጅተውና ታጥቀው ትግል እናካሂዳለን የሚሉት ቡድኖች ከኢትዮጵያ አንድነት አንፃር እንዴት እንደሚታዩ በመዳሰስ፤ በአፍሪካ ቀንድና በሌሎች አካባቢዎች በተከሰቱት ሁኔታዎች፤ ለምሳሌ፤ የሃገራት መፈራረስ፤ የሽብርተኛነት መስፋፋትና የኃያላን መንግሥታት ሚና በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጫና ምን አስከትሏል፤ ያስከትላል እና የወደፊቱ የትግል ስልታችን ምን መሆን አለበት... ወዘተ በሚሉት ላይ ነው።

የይስሙላውን “ምርጫ” በተመለከተ ሸንጎ ምርጫው ከመካሄዱ ከአንድ ዓመት በፊት የምርጫው ሂደት ነጻ፤ ፍትሃዊና አግባብ ያለው እንዲሆን ከተፈለገ ዘጠኝ ነጥቦችን ያቀፈ ቅድመ ሁኔታዎችና ዝግጅቶች መሟላትና መተግበር እንደነበረባቸው ገልጾ ነበር፡፤ ሆኖም አንዳቸውም ስራ ላይ እንዳልዋሉ አስታውሶ፤ ጉባዔው ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው ኢህአዴግ የመንግሥት ለውጥ በምርጫ እንዲካሄድ የማይፈቅድና በሕገ መንግሥቱ መመሪያ መሰረት የሚደረገው የሰላማዊ ትግል ጭላንጭል ሙሉ በሙሉ እንደተዘጋ ተስማምቶበታል። በሕገ መንግሥቱና በዓለም ህጎች መሰረት የመንግሥት ለውጥ በሰላም ሊደረግ አይችልም ብሎ ጭካኔውን፤ አፈናውን፤ ግድያውንና ማሳደዱን ከመቸውም በሚዘገንን ደረጃ የሚያካሂደው ህወሓት የሚያዘውና የሚቆጣጠረው ኢህአዴግ የሚያሳየው ባህርይና ድርጊት ካለፉት ስህተቶች ሊማር አለመቻሉን፤ የበላይ አለቆቹና ተተኪዎቹ ራሳቸው በፈጠሩት የጥላቻና የቂም በቀል ርእዮት ተበክለው በፍርሃት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ መሆኑን፤ ይህ ፍርሃት መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የበከለው መሆኑን... ወዘተ ያሳያል።

የማህበረሰብ ሆነ የፖለቲካ፤ የኃይማኖት ሆነ የሰብአዊ መብቶች መከበር ጠበቃ የሆነ ግለሰብና ተቋም ድምፁን ሲያሰማ የሚደርስበት ተከታታይ ክስና የሃሰት መረጃ “ሽብርተኛ ነህ/ነሽ” የሚል ብቻ ነው። በጥላቻና በቂም በቀል የተበከሉት የህወሓት መስራቾችና ተተኪዎች በተደጋጋሚ ሊያስታውሱን የሚሞክሩት ሃቅ “እኛ በትጥቅ ትግል መስዋእት ከፍለን ያገኘነውን ስልጣን” ልትነጥቁን የምትችሉት እናንተም ተመሳሳይ ትግል አካሂዳችሁ ብቻ ነው የሚል እብሪተኛና ትምክህተኛ የሆነ ብሂል ነው። ይህ አብሪትና ትምክህተኛነት ሁለት የማያሻሙና መፈታት ያለባቸው ችግሮችን ያንፀባርቃሉ፤

አንድ፤ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የመንግሥት አመራርና ስርዓት ለውጥ ወይንም ሽግግር በሰላም ሊተገበር አለማቻሉን፤ ይኼም ለዲሞክራሲ ምስረታ ማነቆ መሆኑን፤

ሁለት፤ በሃገር ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነትና በውጭ ወረራ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ በህይወቱና በኃብቱ ብዙ መስዋእት መክፈሉ፤ መራቆቱ፤ መድከሙ፤ መማረሩ፤ ክብሩን መገፈፉ፤ ሉዐላዊነቱና ትሥስሩ መውደሙ ናቸው።

ጉባዔው ይኼ ዑደት (Cycle) እና ሁከት (Cycle of Violence) ልክ እንደ ተራ ነገር የተለመደ መሆኑ ለሃገራችን ህልውና ዘላቂነትና ለስብጥር ሕዝቧ አብሮና ተቻችሎ ማደግና መኖር ፀር መሆኑንና አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ መክፈት ብልህነት መሆኑን ተስማምቶበታል። አዲስ ፖለቲካ ስንል፤ ከጥላቻና ከቂም በቀል የፖለቲካ ባህል ወደ መቻቻል፤ መወያየት፤ መከባበር፤ መደማመጥ፤ አብሮ ችግሮችን ወደ መፍታት፤ መደጋገፍ... ወዘተ ባህል እንዙር ማለታችን ነው። የህወሓት/ኢህአዴግን የጥላቻ ባህል ይዘን ዲሞክራሳዊ ስርዓት ልንመሰርት አንችልም።

ህወሓት ይኼን የተያያዘ ጊዜ ያለፈበት የጥላቻና የቂም በቀል ፖለቲካ ባህል ይዞ መቀጠሉ ለተገንጣዮችና ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ ለሚመኙ የውጭ ኃይሎችና ለሽብርተኛነት በር ከፍቷል። የይስሙላው ምርጫ ያባባሰው ይኼን የማይካድ ሁከት ነው። ይኼን በተመለከተ፤ ኢትዮጵያን አፍኖ ለሚገዛው  ቡድን አሳፋሪ ሁኖ ያገኘነው ክስተት ገዢው ፓርቲ ከ547 የፓርላማ ወንበሮች “424 አሸንፊያለሁ” ብሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማቅረቡ ብቻ ሳይሆን የቀሩትን ወንበሮች ራሱ ለፈጠራቸው፤ ታማኝና ታዛዥ ለሆኑ ተጠላፊ ፓርቲዎች መስጠቱ ነው። የዛሬ አምስት ዓመት “በ 99.6” አሸነፍኩ ያለውን የዓለም ሕዝብ ያልተቀበለውን ውጤት ከፍ አድርጎ “መቶ በመቶ አሸነፍኩ” ሲል ስርዓቱን በሕዝብ ድምፅና በሰላም ለመለወጥ አትችሉም የሚል የማያሻማ መልእክት አቅርቦልናል።

ስለሆነም፤ የጉባዔው ዘገባና ድምዳሜ አንድና፤ አንድ ብቻ ነው። ይኼውም፤ ሕግ መንግሥቱ የሚፈቅደው የምርጫ ሂደትና ለሃገሪቱ ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለው የተቋቋሙት ተቋሞች--የምርጫ ቦርድ፤ ፍርድ ቤቶች፤ የፌደራል ፖሊስ፤ መገናኛ፤ ደህንነት፤ መከላከያ...ወዘተ--ለገዢው ፓርቲ ማፈኛና መቆጣጠሪያ፤ መቆያና የኃብት ማካበቻ መሳሪያዎች ሁነዋል የሚል ነው። የምርጫ ቦርድ የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑን በተደጋጋሚ አይተናል። በአለፉት አምስት ምርጫዎች ህወሓት/ኢህአዴግ ከዓለም የምርጫ መስፈርቶች ጋር የተጻረረ፤ እውነተኛ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያፈራረሰ፤ መሪዎችን ያሳደደ፤ ያሰረና፤ ምርጫውን ካሸነፈ በኋላም የገደለ፤ በመግደልና በማሳደድ ላይ ያለ፤ የሕዝብ እምቢተኛነት ሲከሰት ችግሩን ሁሉ በአፈናና በመሳሪያ ኃይል እፈታለሁ የሚል አምባገነናዊ አገዛዝ ሆኗል። በአጭሩ፤ ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው አገዛዝ ሃገሪቱን ለከፋ አደጋ ያጋለጠና የእርስ በእርስ ጥላቻና እልቂት እንዲካሄድ ያመቻቸ ሆኖ አግኝተነዋል።

በጉባዔው ዘገባ፤ ዲሞክራሳዊ ለውጥ ጊዜ የማይሰጥ አስቸኳይ ጉዳይ ሆኗል። ጉባዔው ለማጠናከር የፈልገው መልእክት፤ ህወሓት የሚያካሂደው “የከፋፍለህ ግዛው”፤ የብሄር/ብሄረሰብና የኃይማኖት ጥላቻና ጎሳዊ አድልዎ ለሃገራችን አንድነትና ሉዐላዊነት” እና ለመቶ ሚሊዮን ሕዝቦቿ ሰላም፤ ደህንነት፤ አብሮና ተሳስሮ መኖር ዋናው አደጋ ፈጣሪ ሆኗል። ለማጠናከር፤ ጉባዔው ከዚህ ዘገባና ድምዳሜ ለመድረስ ያመዛዘናቸውን አደገኛ ሁኔታዎች በአጭሩ እናቅርባለን።

ሌላውን ሁሉ መረጃ ወደ ጎን ትተን፤ ባውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት “የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ዓመታዊ” ሪፖርትን፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ (2014) የወጣውን  የ አሜሪካ ኢንተለጀንሰ መስሪያ ቤት ያዘጋጀውን ዘገባ( “U.S. National Intelligence Council Documentary on the TPLF”) እና መንግስታዊ ያልሁነው ፈንድ ፎር ፒሰ (The Fund for Peace, )  በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኙ መንግስታት (“Failed and Failing States”  ) በሚል ያቀርቧቸውን አስጊ ሁኔታዎች እንጠቅሳለን።

አንድ፤ የገንዘብና የተፈጥሮ ኃብት ዘረፋ--ህወሓት እንደ ፓርቲ የሚቆጣጠራቸውና የፈጠራቸው የኢኮኖሚና የፋይናንስ ተቋሞች--ለምሳሌ ኤፈርት የተባለው ሞኖፖሊ፤ በበላይነት የሚቆጣጠረው መንግሥት፤ ጥቂት ምርጥ ግለሰቦች፤ የስለላ፤ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ የበላዮች አብዛኛውን ዘመናዊ ኢኮኖሚ ተቆጣጥረውታል። የጠባብ ጎሳ የበላይነትን ከኢኮኖሚና የተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነትና የበላይነት ጋር አጣምረውታል። ገቢና ኃብት የሚገኝባቸውን ምንጮች ሙሉ በሙሉ የራሳቸው የግልና የቡድን አድርገውታል። ህወሓት የነጋዴዎች፤ የኪራይ ሰብሳቢዎች፤ የአትራፊዎችና የዘራፊዎች ስብስብ ቡድን ሆኗል። ሌላውን “አጥፊ ተቃዋሚ” እያለ በመወንጀል እራሱ ወንጀለኛ ከሆነ አመታት አልፈውታል።

ይኼን ነው፤ ዶኪውሜንተሪው “Ethnocracy combined with Plutocracy” ኢትዮጵያ በዓለም እርዳታ ከሚያገኙ ሃገሮች መካከል አራተኛውን ደረጃ፤ በአፍሪካ አንደኛውን ደረጃ ይዛ ሕዝቧን ለመመገብ አልቻለችም። ከሚለገሰው ግዙፍ እርዳታ ምን ያህሉ ድህነትን ለማጥፋት እንደሚውል አናውቅም። የምናውቀው የህወሓት የበላዮችና ጥቂት አጋሮቻቸው ታይቶ የማይታወቅ ድርጅታዊ ምዝበራ እያካሄዱ፤ ኃብት እንዳካበቱና በልጆቻቸውና በሌላ ዘዴ ብዙ ቢሊየን ዶላር ከሃገር እንዳሸሹ፤ የግል ኩባንያዎች እንዳቋቋሙ ተደርሶበታል። Global Financial Integrity, 2000-2009 ባወጣው ዘገባ $11.7 ቢሊዮን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተሰርቆ ወደ ውጭ ተልኳል፤ በዚህ ዓመት መጀመሪያ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት እምቤኪ የመራው ግብረ ኃይል ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የሸሸው $10 ቢሊየን ነውህወሓት የማይክደው $21 ቢሊየን ዶላር ከሃገር ተሰርቆ ሸሽቷል። ስንት የስራ እድል ይፈጥር ነበር? ለዚህ ተጠያቂው ማን እንደሆነ አከራካሪ አይሆንም።

ሁለት፤ የዘር ፍጅት፤ ማጽዳት ዘመቻ (Genocide and ethnic cleansing)-- የህወሓት  መሪዎችና ተተኪዎች ሌሎች ጠባብ ጎሰኞችን አሳምነው በአማራው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የተቀነባበረና ተከታታይ የዘር ፍጅት ዘመቻ አካሂደዋል፤ አሁንም እያካሄዱ ነው። የብሄር ጥላቻን እንደ ትግል ስልት ተጠቅመው ሌላውን በጥላቻ በክለውታል። ወጣቱ ትውልድ እንዲያምን የተገደደው ጥላቻን፤  የራስን ጥቅም የበላይነት...ወዘተ እንጅ አገራዊና ብሄራዊ ፍቅርንና ጥቅምን አይደለም።

ህወሓት ከጅምሩ፤ የትግራይን ሕዝብ “ያዳከመው፤ ያደኸየው፤ ያገለለውና ያጠቃው የአማራው ብሄርረሰብ ነው” በሚል ብሂል፤ የጥላቻ ጦርነት ሲያካሂድ ቆይቷል። ዘገባዎችና መረጃዎች የሚያሳዩት በጅጅጋ፤ በደቡብ ሸዋ፤ በጉራ ፈርዳ፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ በጋምቤላ፤ በወልቃይት ጠገዴና ሌሎች ቦታዎች የሚዘገንንና በፍርድ የሚያስጠይቅ ፍጅት አካሂደዋል። የራሱ የገዢው ፓርቲ የሕዝብ ቆጠራ ያሳየው ቢያንስ ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሽህ የአማራ ሕዝብ በጥቂት አመታት ውስጥ የት እንደደረሰ አይታወቅም፤ ሌሎች (ለምሳሌ ኢኮንሚስቱ ዶር ብርሃኑ አበጋዝ በምርምር የተደገፈ ማስረጃ) ይኼ ቁጥር ከአምስት ሚሊየን በላይ ሕዝብ መሆኑን ያሳያል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህ ሕዝብ የት ደረሰ፤ ተሰደደ፤ ተገደለ፤ ማንነቱን እንዲለውጥ ሆነ? ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂው ማነው? በኛ አመለካከት ህወሓትና አጋሮቹ መሆናቸው አያከራክርም።

በተጨማሪ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ችግሮችን በሰላምና በመደራደር በመፍታት ፋንታ በአኟክና (2003)፤ በኦጋዴን ኢትዮጵያዊ ሶማሌ ሕዝብ ላይ (በተደጋጋሚ)፤ የሚዘገንን፤ በቪዲዮ የተቀረጸ በፌደራል ፖሊስ የተመራ በዘር ፍጆት የሚመደብ ወንጀሎች ፈጽሟል። በተጨማሪ፤ በተራው የጋምቤላ፤ የኦሞ ሸለቆና ሌሎች ነዋሪዎች ላይ ሂውማን ራይትሰ ዋች፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ፣ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ፣ ጋርዲያን ጋዜጣና ሌሎቹም (Human Rights Watch, Genocide Watch, Amnesty International, International Rivers, Oakland Institute, the Guardian and others) የመዘገቡት የመሬት ነጠቃና ከዚህ ጋር የተያያዘው ነዋሪዎችን ከቀያቸው የማባረር ወንጀል በተደጋጋሚ ተፈጽሟል። ገዢው ፓርቲ እነዚህን የመሳሰሉ ወንጀሎች ሲፈፅም “በልማትና በፀጥታ አስፈላጊነት” ስም ነው። በተጨማሪ፤ እየለየ በድብቅ የሚገድላቸው፤ የሚያስራቸው፤ የሚደበድባቸው፤ ንበረታቸውን የሚገፋቸው፤ እንዲሰደዱ የሚያስገድዳቸው የሃገር ፍቅር ያላቸውን፤ ደፋሮቹን፤ መሪ ለመሆን ብቃት ያላቸውን፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የቆሙትን ነው። ምርጫውን “አሸነፍኩ” ካለ በኋላ የገደላቸው ደፋርና አገር ወዳድ መሪዎች ምን ወንጀል ሰሩ? ማን ገደላቸው፤ በማን ትእዛዝ? የገደሉት ለምን አልተያዙም? የተገደሉበት ዋና ምክንያት ለህወሓት ተወዳዳሪ የሆነ አገር ወዳድና በፍትህ የሚያምን ትውልድ እንዳይፈጠር መቀጣጫ ለማድረግ ነው።

ሶስት፤ የሰብዓዊ መብቶች፤ የኃይማኖትና የፕሬስ ነጻነት አፈና--- ከላይ እንዳቀረብነው፤ ያለፈው ምርጫ የፖለቲካ ምህዳር መዘጋት ነፀብራቅ ነው። አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ ፍሪደም ሀውስ፤ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ሲፒጄ ያሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፡ የአውሮፓ ማህበርና ሌሎችም የሚጋሩት የኢትዮጵያ አገዛዝ ለማህበራዊ (ለሰብአዊ) መብቶች ፀር መሆኑንና ይኼ ሁኔታ ከቀጠለ ለሃገሪቱ መፈራረስና ለእርስ በእርስ ጦርነት መዘዝ መሆኑን ነው። ሲፒጄ (CPJ) ባደረገው ጥናት መሰረት “ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማፈንና ከሃገር እንዲለቁ በማድረግ፤ ከዓለም አራተኛ፤ ከአፍሪካ ሁለተኛ” መሆኗን በተደጋጋሚ አስምሮበታል። ሽብርተኛ ተብለው ከታሰሩት መካከል እስክንድር ደስታ፤ ተመስገን ደሳለኝ፤ ውብሸት ታየ፤ አንዱ ዓለም አራጌ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ አቡበከር አህመድ፤ አብርሃ ደስታ፤ የሸዋስ አሰፋ፤ ዳንኤል ሽበሽና ሌሎች ብዙ ሽዎች የፖለቲካ እስረኞች ይገኙበታል። ቢያንስ ሰባ ዘጠኝ ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል፤ ይኼ “በዓለም የመጀመሪያውን ደረጃ” የያዘ ሃቅ ነው። ከላይ የጠቀስነው ዶኪሜንተሪ እንዳሳየው  የኢትዮጵያ መንግስት ከጋዳፊና ባለማችን ከታዩት ሌሎችም ጨካኝ አምባገነኖች የማይለይ መሆኑን ነው

ህወሓት ሁሉንም ተቋሞች ለመቆጣጠር በተከተለው ዘዴ መሰረት፤ ስልጣን በያዘ ማግስት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኃይማኖትን አመራር በቁጥጥሩ ስር እንዲውል አድርጓል፤ አግባብ ያላቸውን ፓትሪያርክ አስወግዶ ለህወሓት ታዛዥና ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ሹሟል። እንደ ዋልድባ ያሉ የማይተኩ ገዳሞችን ህልውና ለማሳጣት ሞክሯል፤ የዋልድባ አባቶችና እናቶች የሚተዳደሩበትን መሬት ለስኳር አገዳ ማምረቻ እንዲውል አድርጓል። ኃይማኖትን የፖለቲካ የበላይነት መሳሪያ ማድረግ ለሃገሪቱ አደጋ ፈጥሯል፤ ለውጭ ኃይሎች መግቢያ ቀዳዳ ሆኗል። በተመሳሳይ፤ የእስልምና ኃይማኖት አመራር ህወሓት በሚፈልገው መንገድ እንዲቋቋምና እንዲመራ አድርጓል፤ መሪዎችንና አባላትን አስሯል።

ገዢው ፓርቲ አስደናቂ እድገት እያሳየሁ ነው በሚላት የምግብ ጥገኛ ሃገር፤ ለወጣቱ ትውልድ የስራ እድል ለመፍጠር አልተቻለም። ዛሬ ሃገሪቱ ከምትታወቅባቸው አንዱ ወጣቱ ትውልድ በተከታታይ መሰደዱ ነው። በየዓመቱ፤ ብዙ ሽህ ወጣቶች በጅቡቲ፤ በሶማሊያ፤ በሰሜንና ደቡብ ሱዳን፤ በኬንያ ወይንም የመውጫ ፈቃድ አግኝተው በቦሌ ወደ ውጭ ይሰደዳሉ። ከወጡ በኋላ የህወሓት/ኢህአዴግ  አገዛዝ መብታቸውን አያስከብርም። የኢኮኖሚው አመራር በሕዝብ የበላይነት የሚመራ ካልሆነ፤ ሕዝብን የእድገት ማእከል ካላደረገና የእድገቱ ውጤት ለሕዝብ አገልግሎት ካልዋለ የኑሮው ቀውስና ስደቱ አያቆምም።

አራት፤ ከመንግሥት ባለቤትነት የመነጨ የመሬት ነጠቃ---አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚተዳደረው በእርሻና ተመሳሳይ ስራ ነው። በገጠር ሆነ በከተማ የመሬት ባለቤትነት የዜግነት መታወቂያና የኑሮ መመኪያ ነው። ህወሓት በበላይነት የሚመራው አገዛዝ የተፈጥሮ ኃብትን በሙሉ “የመንግሥት ነው” በሚል ዘዴ መሬትን ለንግድና ለግል ጥቅም አውሎታል። የመሬት ቅርምት (Land Grab) ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያውያንን አንጡራ የተፈጥሮ ኃብት ለውጭ አገር ኢንቬስተሮች ቸርችሮታል። ሳውዲ ስታር፤ የህንዱ ካሩቱሪ፤ ሩች ሶያ፤ የህንድ ድንች አምራቾች ተቋምና ሌሎች ጋምቤላን ሙሉ በሙሉ ተቀራምተውታል ለማለት ይቻላል። ብዙ ሚሊየን ሄክታር ለም መሬትና ወንዝ ለውጭና በሃገር ቤት ታማኝ ለሆኑ አትራፊዎች ተቸርችሯል። በጋምቤላ ብቻ የታወቀው ለውጭ ኢንቬስትሮች የተሰጠውና የግል የሆነው መሬት በዝቅተኛ 650,000 ሄካታር በከፍተኛ 2,000,000 ሄክታር ይደርሳል። የከተማና የገጠር መሬት ለግል ትርፍና ለሙስና ቁልፍ ሆኗል። በከተማ ቦታ ምደባ፤ ስደተኛውም ተጠቃሚ ሁኖ የከተማ መሬትን ዋጋ የማይቀመስ አድርጎታል። ይኼ በፖለቲካ የበላይነት የሚወሰን የመሬት አስተዳደር ሁኔታ እስካልተለወጠ ድረስ ፍትሃዊ የሆነ የመሬት አጠቃቀም ሊኖር አይችልም።

አምስት፤ የስለላ፤ የደህንነት፤ የመከላከያ፤ የፍርድና የፌደራል ፖሊስ ፍፁም የበላይነት ---እነዚህና እንደ ጉምሩክ፤ መገናኛ ቁልፍ ሚና ያላቸው ተቋሞች የሚያገለግሉት ህወሓትን ነው። የፓርቲው ተቀጥላዎችና አገልጋዮች ከሆኑ ቆይተዋል። በ2009 የተገኘ መረጃ ያሳየው ከጠቅላላው የኢትዮጵያ የመከላከያ እዝ አስራ ሰባቱ ጀኔራሎችና አርባዎቹ ኮሎኔሎች የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፤ አንድ የአገው ተወላጅና አንድ የአማራ ተወላጅ ጀኔራሎች ነበሩ። አንድም የኦሮሞ ጀኔራል የለም፤ በኮሎኔል ደረጃ ሌሎች ብሄረሰቦች አልተወከሉም። በፖለቲካው፤ በኢኮኖሚው፤ በባንኩና ፋይናንሱ፤ በመገናኛው፤ በአስተዳደሩ፤ በደህንነቱ፤ በመከላከያው፤ በፌደራል ፖሊሱ፤ በጉሙሩኩ ዘርፎች የፖሊሲና የውሳኔ ኃላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እንደዚህ አይን ያወጣ አድልዎ የትም ሃገር አይታይም።

ቢያንስ ዘጠና አምስት በመቶ የሚሆነው የደህንነቱን፤ የፌደራል፤ የልዩ ፖሊሱንና የመከላከያውን እዝ በበላይነት የሚመሩት ለህወሓት ታማኝ የሆኑ የትግራይ ብሄረሰብ አባላት ናቸው። ይኼ አይን ያወጣ  አድልኦ መሆኑ አያከራክርም።  ይኼ ለበላይነት የተዋቀረና እጅግ ጠባብ የሆነ  አመራር ለሃገሪቱ ደህንነትና ዘላቂነት፤ ለሕዝቧ ሉዐላዊነትና አንድነት፤ ለሕግ የበላይነትና ለዴሞክራሲ አደገኛ መሰናክል ፈጥሯል።  ህወሓት ይኼን የበላይነት ያጠናከረው ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተቋሞችን በማውደም፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በማጥፋት፤ የትምህርት ይዘቱን ክልላዊና ጎሳዊ በማድረግ፤ አገር ወዳድ የሆኑ መምህራንን በማባረር፤ የጥላቻ ባህል ጥልቀትና ስፋት ይዞ አዲሱ ትውልድ እርስ በእርሱ እንዳይተማመንና ብሎም እንዲጋጭ በማድረግ ነው። ዛሬ ልክ ዩጎስላቪያ እንደሆነው፤ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያያይዙ ባህሎችና ልምዶች በህወሓት ወድመዋል ለማለት እንችላለን። ይኼ ሁኔታ ለእርስ በእርስ ግጭት፤ ለዘር ፍጅት፤ ለተገንጣይ ኃይሎችና ለውጭ ጠላቶች የጥቃት መግቢያ ሆኗል።

ስድስት፤ የውጭ መንግሥታት፤ በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ሚና አሳሳቢነት--የምእራብ ሃገሮች፤ በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ከሰብዓዊ መብቶች መከበር ይልቅ ለመረጋጋትና ለፀረ-ሽብርተኛነት ዘመቻ ቅድሚያ እየሰጠ አምባገነኑን የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ መደገፉ ለራሱ ጉዳት እንዳመጣ እናምናለን። የኢትዮጵያና የአሜሪካ ከመቶ አስር ዓመታት በላይ የቆየ ግንኙነት አስተማማኝ በሆነ ደረጃ ሊቀጥል የሚችለው አፋኙን አገዛዝ በማውገዝና የሚሰጠው የገንዘብና ሌላ እርዳታ እንዲቆም በማድረግ እንጅ ድጋፉን በመቀጠል አይደለም። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ቀውስ ውስጥ መግባት፤ መባባስ፤ የሰብአዊ መብቶች መረገጥ፤ የኃይማኖት ነጻነት መታፈን፤ በፀረ-ሽብርተኛነት ሽፋን የገዢው ፓርቲ ሕዝብ አሸባሪ መሆን፤ የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ መባከን፤ ከመቶ በላይ የሚገመቱ በጎሳ የተደራጁና የታጠቁ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሃገሪቱ ሁኔታ ተባብሶ የመገንጠል ዓላማቸውን ስኬታማ ለማድረግ መዘጋጀት፤ ለልማት መዋል የሚችል ግዙፍ የሆነ ኃብት ከሃገር እየሸሸ መውጣቱ...ወዘተ ለአሜሪካም ዘላቂ “ጥቅም” ጉዳት እንደሚያመጣ እንገምታለን። ለዚህ አግባብ ያለው፤ የማያሻማ መልእክት ለኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ መስጠት ነው።

ጉባዔው በቅርቡ ሸንጎ ለፕሬዝደንት ኦባማ የጻፈውን ግልፅ ደብዳቤ መሰረት አድርጎ፤ የአሜሪካ መንግሥት ለሚከተሉት መተክሎች (Principles) እና እሴቶች ትኩረት እንዲሰጥ የዲፕሎማቲክ ዘመቻ ማካሄድ ይኖርበታል በሚል ተስማምቷል።

አንድ፤ የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ ብሎገሮችና የኃይማኖት መሪዎችና ተከታዮች በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ ጥቂቶቹን ለይስሙላ ፈትቶ ሌሎችን እያሰቃየ ነው፤

ሁለት፤ የመገናኛ ብዙሃን፤ የኃይማኖት፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመንቀሳቀስና የመደራጀት ነጻነት እንዲከበሩ፤ የማህበረሰብ ድርጅቶች እገባ እንዲቆም፤ የፀረ-ሽብርተኛው ሕግ እንዲነሳ፤

ሶስት፤ የፍርድ ቤት፤ የፌደራል ፖሊስ፤ የመከላከያና የምርጫ ቦርድ ተቋሞች ከገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሁነው መላውን ሕብረተሰብ እንዲያገለግሉ፤

አራት፤ ነዋሪዎችን ከመሬታቸው እንዲገለሉ የሚደረገው ዘመቻ እንዲቆም፤

አምስት፤ በዘር ፍጅት የሚታወቁ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡና የዘር ፍጅት ዘመቻው በአስቸኳይ እንዲቆም።

ከላይ የቀረቡት መተክሎች አሜሪካ የምታምንባቸው እሴቶች እንደመሆናቸው መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደተግባር ካልተተረጎሙ የአሜሪካ መንግሥት ለህወሓት/ኢህአዴግ የሚሰጠውን እርዳታ በጥንቃቄ መመርመር ይገባዋል። ጉባዔው  ይኼን በሚመለከት የሸንጎ አመራር ለፕሬዝደንት ኦባማ ልዩ ደብዳቤ እንዲፅፍ አሳስቧል።

የትግል ስልት

ከላይ የቀረበውን ኃሳብና አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ጉባዔው ስለ ትግል ስልት ሰፊ ውይይት አድርጎ በሚከተለው ተስማምቷል። ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካውንና የማህበረሰቡን ነጻነት ተስፋ፤ ምኞትና የመንቀሳቀስ ምህዳር ሙሉ በሙሉ በመዝጋቱ በሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መብት መሰረት በሰላም ለውጥ ለማምጣት የማይቻል መሆኑን አምኗል። ጉባዔው፤ ተቃዋሚዎች፤ የተለያዩ የትግል ስልቶች ቢከተሉም፤ ኢትዮጵያን እንታደግ፤ ለአገራዊና ብሄራዊ ስሜት እንታገል፤ መጠላለፍ እናቁም፤ እንደጋገፍና እንተባበር ከሚሉ አገር ወዳድ ከሆኑ የአንድነት ኃይሎች ጋር አብሮ ለመስራት ያደረገውን ጥሪ አሁንም ያድሳል።

ሸንጎ በመግቢያው የቀረቡትን መርሆዎች ስኬታማ ለማደረግ ከዚህ በፊት በተከታታይና በቆራጥነት ያልተሞከሩ የትግል መንገዶች ሁሉ መስተናገድ አለባቸው የሚል እምነት አለው። በተጨማሪ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሲያስተጋባ ከቆየው የብሄር/ብሄረሰብና የኃይማኖት ከፋፋይነት፤ የጥላቻና የቂም በቀል የፖለቲካ ባህል ወደ ዴሞክራሲያዊ ባህል መሸጋገር ወሳኝ መሆኑን እናምናለን።

ምንም እንኳን የሃገሪቱ የተፈጥሮ ኃብትና እድገት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥቅም ይዋል፤ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች ይከበሩ፣ የሀገር አንድነት ይጠበቅ...ወዘተ የሚል እምነት ይዘው ገዢውን ፓርቲ  ሲታገሉ ብዙ ታጋዮች ቢገደሉም፤ ቢታሰሩም፤ ቢደበደቡም፤ ከሃገር ቢሰደዱም፤ አሁንም በሃገር ቤት ሁነው የሚታገሉ አገር ወዳድ፤ ደፋርና ለውጥ ፈላጊዎች ብዙዎች ናቸው። እነዚህን ደፋር፤ ቆራጥና አገር ወዳድ  ወገኖቻችንን በማንኛውም መንገድ መደገፍ አቅማቸውንም ለመገንባት በሚያደርጉት ጥረት ማገዝ  አስፈላጊ ነው።

በመርሆዎቻችን መሰረት ኢትዮጵያውያንን ያማከለና ያሳተፈ  የተጠናከረ ሰላማዊ ትግል እንዲካሄድና አፋኙ አገዛዝ በዴሞክራሲያዊ  አስተዳደር እንዲተካ ያልተቆጠበ ጥረት እናደርጋለን።  በሰላማዊ ትግል እናምናለን የሚሉ የፖለቲካ፤ የማህበረሰብ፤ የኃይማኖት፤ የሞያና ሌሎች ድርጅቶች፤ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች የሚያካሂዱት ትግል ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የዓላማ አንድነት ተከትለው (ተከትለን) በትግል ስልት የተለያዩትንም ሲያካትቱ (ስናካትት) ነው። ጉባዔው የተለያዩ የትግል ስልቶች መኖራቸውን ተቀብሎ የትግሉን ዘላቂነትና ውጤታማነት የሚወስነው ሕዝብን ማእከል፤ አጋርና አሳታፊ ማድረግ ከቻለ መሆኑን አስምሮበታል። ሕዝብን ያሳተፈ፤ ሕዝብ በባለቤትነት የያዘው ትግል በምንም ሊጠቃ አይችልም። ዴሞክራሲያዊ  አስተዳደር አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው የሕዝብን አመኔታ ሲያገኝ ብቻ ነው የሚለውን ግብ ጉባዔው ተቀብሎታል። ትግሉ በከተማና በገጠር የተያያዘና የተቀነባበረ እንዲሆን ድርሻችን ከመወጣት ወደ ኋላ አንልም።

ለሰላማዊ ትግሉ ውጤታማነት  የሚጠቅመው የተሳሰረና የተቀነባበረ አመራር ያለው አገር አቀፍ እምቢተኛነት ነው የሚል እምነት አለን።  ለምሳሌ፤ ከተሜው፤ ገጠሬው፤ ወጣቱ፤ አዛውንቱ፤ ድሃው፤ ባለ ኃብቱ የተባበረበት የየካቲትን ወይንም የግንቦት ዘጠና ሰባትን የሚመስል የሕዝብ እምቢተኛነት ትግል፤ አንዱ ወገን ሲጠቃ ሌላው ድምፅ የማሰማት ትግል፤ የስራ ማቆም አድማ፤ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ የግል የንግድ ተቋሞች እቀባ፤ በሃገር ቤትና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች የዲፕሎማሲ ትብብር ገዢውን ፓርቲ የማጋለጥ ዘመቻ፤ የተጠናከረ የዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን ተጠቅሞ ህወሓት/ኢህአዴግ ወጣቱን ትውልድ የሃገሩን ታሪክ፤ የጀግኖቿን ጀብዱ ስራ፤ የሕዝቡን ተቻችሎ መኖር ወዘተ የሃሰትና የሰው ሰራሽ ታሪክ መሰሪነት አውቆ ለሃገሩና ለወገኑ ተባብሮ የሚነሳበት ዘመቻ፤ በውጭ የሚገኘውን የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ የማጋለጥና ሰላዮችን ለፍርድ የማቅረብ ዘመቻ፤ ከሃገር ተሰርቆ የሸሸውን ኃብት የማጋለጥና የማስመለስ ዘመቻ፤ በጥናትና ምርምር የተመሰረተ የእርቅና የሠላም ድርድር ዘመቻ፤ የአንድነት ኃይሎች መተባበርና ውጤት የሚያስገኝ ትግል ዘመቻ ወዘተ። እነዚህና ሌሎች በተከታታይነት ያልተሞከሩ የትግል ዘርፎች ናቸው። የህወሓት/ኢህአዴግን ፈቃደኛነት አይጠይቁም። ከላይ እንዳሳየነው፤ እብሪተኛው ገዢ ፓርቲ ለእርቅና ለሰላም የሚደረግ ጥሪን እንደማያስተናግድ እናምናለን። ሆኖም፤ ጥረቱ በጥላቻ፤ በቂም በቀልና በራስ ወዳድነት ለተበከለው የአዲስ ትውልድ ክፍል ትምህርታዊ ግብዓቶችን ያበረክታል፤ የዓለምን ሕብረተሰብ ልቦና ያንቀሳቅሳል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥት ለውጥ በመሳሪያ ብቻ እንጅ በመወያየትና በመደራደር አይታሰብምና ተቃዋሚዎች የሚፈልጉት ዲሞክራሲን ሳይሆን ስልጣንን ነው የሚለውን ከእውነቱ የራቀ  የህወሓት/ኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ የማይቀበሉ የአንድነት ኃይሎች እንዳሉ ያሳያል። እነዚህን ሁሉ ለማድረግ ቆራጥነትና ተባባሪነት ያስፈልጋል፤ በፅሁፍ መቅረባቸው ብቻ በቂ አይደለም።

በትጥቅ መንገድ እንታገላለን ከሚሉት ውስጥ ከዓላማችን ጋር የሚመሳሰል ዓላማ ካላቸው ጋር መተባበር እንዳለብን ጉባዔው ተወያይቶ ተስማምቷል። ሆኖም፤ ሁሉም በትጥቅ ትግል ህወሓት/ኢህአዴግን የሚፈታተኑት ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ዘላቂነትና ጥቅም፤ ለመላው ሕዝቧ ሉዐላዊነት ትሥስርና እውነተኛ እኩልነት፤ ለፍትህና ለሕግ የበላይነትና ሁሉን የማህበረሰብ ክፍሎች ለሚወክል ዲሞክራሳዊ ስርዓት ይታገላሉ ማለት አይቻልም። በዚህ አኳያ ልናስብበት የሚገባን  ያለፈው የፖለቲካ ሂደት አንዱ ትምህርት አንድ አምባገነን አስወግዶ ሌላ አምባገነን መተካት እንዳይከተል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያሰፈልግ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግን በመጥላት ከታጠቁ ተገንጣይ ኃይሎች የሚከሰተውን የኢትዮጵያን መፈራረስ፤ አደጋ የእርስ በእርስ ግጭትና የዘር ፍጅት ሴራዎች ሙሉ በሙሉ እንቃወማለን።

ኤርትራን በተመለከተ

ኤርትራ ከጥንቱ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኣካል የሆነች ክፍለ-ሃገር ነች። ከ1890ቹ ጀምሮ ክፍለ-ሃገሪቱ የብዙ ፖለቲካ ምስቅልቅሎችና የትጥቅ ትግሎች ሰለባ ሆና እንደቆየች ኣይካድም። በዚህ ሂደት ህዝቡ የዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮ ስለመፃኢ ዕድሉ በነፃነት ሊወስንበት የቻለበት ሁኔታ ከተውንም አላገኘም። በ1993 (እ.አ.አ) በኢሳያስ ኣፈወርቂና በመለስ ዜናዊ ኣቀነባባሪነት ኤርትራ ተገንጥላ ‘ነፃ’ ሃገር እንድትባል መደረጉ የዚሁ ሂደት ኣካል ነው። ተካሄደ የተባለው ሬፈረንደም ተቃዋሚዎችን ያላሳተፈ፤ ህዝቡንም ምርጫ የሌለው ውሳኔ እንዲቀበል ያስገደደ፤ በጠብመንጃ ግፊት የተፈፀመ በመሆኑ ተቀባየነት የለውም። ስለዚህም ሸንጎው ኤርትራን እንደ ‘ነፃ’ ሃገር ሳይቀበል የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እስኪመሰረት ድረስ ትግሉን ይቀጥላል።

ብሄራዊ መግባባት እርቅና ሰላም

በህወሓት ላይ የሚደረገው ልዩ ልዩ ትግልና ጫና እንዳለ ሆኖ፤ ጉባዔው ሰፊ ምርምርና ጥናት አድርጎ፤ ከህወሓት/ኢህአዴግ የጥላቻና የጎሳ ፖለቲካ ወደ ነጻና ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ወደሚያሳትፍ ብሄራዊ መግባባት እርቅና ሰላም ውይይት መሸጋገር ለዴሞክራሲ ወሳኝ መሆኑን ተቀብሏል። ምንም እንኳን እብሪተኛው ህወሓት ለዚህ ዓይነቱ ድርድር ዝግጁና ፈቃደኛ አለመሆኑን ብናውቅም፤ የእርቅና ሰላም ጽንሰ ሃሳብ በሃገር ቤትና በውጭ ከፍተኛ ውይይት እንዲካሄድበት ጉባኤው አሳስቧል። ሸንጎ ለዚህ ለተቀደሰ አማራጭ ያልተቆጠበ ድጋፍና እርዳታ ያደርጋል።

በመጨረሻ ጉባዔው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያቀርበው አደራ፤ ለኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለፍትህ፤ ለሕግ የበላይነት፤ ለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት...ወዘተ ስኬታማነት እውን የሚሆነው በጋራ ዓላማ ላይ የተመሰረተ፤ የተቀነባበረ ሕዝባዊ ትግል ሲካሄድ ብቻ እንደሆነ ነው። ህወሓት ሊያፈራርሳቸው ቢሞክርም፤ አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የአንድነት ዘርፍና አካል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወሳኝ የሆነ ሚና ለመጫወት ስለሚችሉ ኢትዮጵያን ሆሉ የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፋችሁን ለግሷቸው፤ እኛም የተቻለንን እናደርጋለን እንላለን።  በተመሳሳይ፤ ሸንጎ በሃገር ቤትና በውጭ ከሚታገሉ የአንድነት ስብስቦችና ግለሰቦች ጋር ተባብሮ ለመስራትና ለመታገል ዝግጁ መሆኑን በድጋሜ ቃል ይገባል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

 

 

Hits: 1391

Joint Letter to President Obama on Ethiopia and Kenya

 

President Barack Obama

The White House

1600 Pennsylvania Avenue NW

Washington, DC 20500

Dear Mr. President:

We welcome your decision to visit sub-Saharan Africa once again, and we applaud your support for African human rights defenders through your Stand with Civil Society initiative. The U.S.-Africa Leaders Summit held last year demonstrated your commitment to engage constructively with leaders on a number of key economic, political and security issues. Your upcoming trip to Ethiopia and Kenya offers another timely opportunity to demonstrate America's commitment to helping to build strong democratic institutions to benefit the continent's one billion citizens.

Ethiopia and Kenya face grave and worsening human rights challenges, and we trust those issues will be at the forefront of your discussions. The longstanding crackdown on human rights groups and journalists in Ethiopia and the use of so-called "anti-terror" laws to stifle the legitimate work of civil society actors in both Kenya and Ethiopia underscore their overall failure to adhere to democratic principles and international human rights standards.

For example, in April 2014, six Ethiopian bloggers and three journalists associated with the Zone 9 blogging collective were accused of "creating serious risk to the safety or health of the public" and arrested under the country's vague anti-terrorism law. While we welcome the recent release of five of those arrested, four remain behind bars today. Also, on April 7 of this year, two Kenyan human rights groups, Muslims for Human Rights (MUHURI) and Haki Africa -- with which many international human rights groups and donors have worked for many years -- were officially listed by the government as "Entities Suspected to be Associated with Al-Shabaab." As a result, their bank accounts remain frozen, and the NGO Coordination Board has commenced investigations into these two prominent groups, which may well lead to their deregistration. These recent examples illustrate a much broader and worrying trend in the region that affects the ability of civil society to freely operate without governmental intimidation or harassment.  

We believe it imperative that you take the opportunity of your visits to meet publicly with pro-democracy and human rights activists, especially those at risk. By doing so, you would be affirming your solidarity with them, while demonstrating the concern we know you share regarding the troublesome developments described above. You would also call attention to the need to protect shrinking civic space in Kenya, Ethiopia, and the broader region, thereby sending a strong message that your administration remains committed to integrating human rights and good governance concerns into its official bilateral relations with all nations. Most importantly, meeting with activists will provide them with the necessary protection as they go about working on behalf of the same human rights issues the United States stands behind.

We would be pleased to work with you and your staff on arranging such a meeting during your upcoming trip, including helping to identify civil society groups and other key issues to address.

Thank you for your time and for your thoughtful consideration of these important issues.

Sincere regards,

Front Line Defenders (Global)

Open Society Foundations (Global)

Robert F. Kennedy Human Rights (Global)

World Movement for Democracy (Global)

 

Africa Center for Peace and Democracy (Africa Regional)

Africa Freedom of Information Center (Uganda)

American Jewish World Service (Global)

Atrocities Watch Africa (Africa Regional)

AU We Want Coalition (Africa Regional)

BudgIt (Nigeria)

Bulawayo Agenda (Zimbabwe)

Centre for Constitutional Governance (Nigeria)

Center for the Development of People (Malawi)

Citizens Center for Integrated Development and Social Rights (Nigeria)

Civil Society Associations Gambia

Coalition for Change (The Gambia)

Council for Global Equality (Global)

Counseling Services Unit (Zimbabwe)

East and Horn of Africa Human Rights Defenders Network (East Africa Regional)

FAHAMU-Networks for Social Justice (Africa Regional)

Federation of Women Lawyers (Kenya)

Freedom House (Global)

Gender Awareness Trust (Nigeria)

Grace to Heal (Zimbabwe)

Human Rights Foundation (Global)

Human Rights Watch (Global)

Independent Advocacy Project (Nigeria)

InformAction (Kenya)

Kenyan Section of the International Commission of Jurists (Kenya)

Media Initiative for Open Governance in Uganda (Uganda)

Muslims for Human Rights (Kenya)

National Coalition of Human Rights Defenders (Kenya)

National Coalition of Human Rights Defenders (Uganda)

New Initiative for Social Development (Nigeria)

Open Democracy Advice Center (Global)

OpenTheGovernment.org (Global)

PEN American Center (Global)

Pan African Lawyer's Union (Africa Regional)

Publish What You Pay (Global)

Sexual Minorities Uganda (Uganda)

Shalom Project (Zimbabwe)

Solidarity Movement for a New Ethiopia

State of the African Union (Africa Regional)

Strategic Empowerment & Mediation Agency (Nigeria)

South Sudanese Network for Democracy and Elections (South Sudan)

Sudan Social Development Organization (Sudan)

Zimbabwe Human Rights Association (Zimbabwe)

Zimbabwe Human Rights NGO Forum (Zimbabwe)

 

 

Hits: 806

Open Letter to President Barack Obama

June 22, 2015

To: President Barack Obama, President of the United States

Mr. John Kerry, Secretary of State, United States of America

From: Ethiopian People’s Congress for United Struggle (SHENGO)

Subject: President Barack Obama’s Visit to Ethiopia

“If the dignity of the individual is upheld across Africa, then I believe Americans will be more free as well, because I believe that none of us are fully free when others in the human family remain shackled by poverty or disease or oppression…Governments that respect the rights of their citizens and abide by the rule of law do better, grow faster.”

President Obama, South Africa, June 30, 2013

Dear Mr. President,

The Ethiopian People's Congress for United Struggle (SHENGO) wishes to express deep concern about your decision to visit Ethiopia at a time when the vast majority of Ethiopia’s 100 million people live in an environment of fear, repression, dejection and exclusion by their own government and chronic poverty. The plethora of evidence on the ground shows unequivocally that civil society, independent media and political competition and the chance to set up private businesses and to gain employment on merit have been thwarted by a narrow band of ethnic elites that has captured the state and the national economy. The U.S. Department of State and numerous human rights organizations offer evidence of unprecedented and persistent human rights violations including summary executions and jailing of political leaders and members, the abrogation of the rule of law, the undermining of public trust in their government institutions and public officials. By your own definition, the Ethiopian government is not one that respects the “dignity of individual citizens or respects the rights of its citizens or abides by the rule of law,” values that you echo in public.

SHENGO recognizes the fact that in a region dotted by failed and failing states, internal displacement of millions, unabated migration and human trafficking, endemic poverty and hopelessness, civil conflict and terrorism, the government of the United States considers the Ethiopian government as a reliable ally and friend in the war against terrorism.  History teaches

us that, regardless of the government in power in either country, U.S. and Ethiopian relations span more than 100 years and will endure for generations to come. We are therefore skeptical that, in the long term, the Ethiopian government that suppresses and oppresses its own citizens under the pretext of Anti-terrorism will serve as a bastion of stability by providing the institutional and policy basis for sustainable and equitable growth for Ethiopia’s millions.

Mr. President,

While Africans, including Ethiopians welcome America’s engagement, especially in the advancement of human rights, the rule of law and democracy and in building prosperous societies, we are concerned that your proposed visit to Ethiopia is most likely to do the opposite. It will embolden the single party state that uses Anti-Terrorism and Charities and Societies Proclamations to punish all forms of dissent. Andrew Beatty of AFP put the risks your visit entails succinctly in his comment on June 20, 2015. “U.S. President Barack Obama will in late July become the first sitting American leader to visit Ethiopia and the Headquarters of the African Union” where he plans to “meet with Ethiopian government and AU leaders.” As you know, the African Union is the only organization that served the Ethiopian government by sending an observation team to a make-believe Parliamentary Election best described as a “sham” and a non-event. For this reason and as noted by Mr. Beatty, “human rights groups have questioned the visit to Kenya, but are also asking why Obama is visiting Ethiopia so soon after a contested,” and we add, flawed “election in which the ruling party won 100 percent of the votes” in succession.

Ethiopia’s case is reminiscent of the old Soviet system; and your visit will be taken as an approval that the single party state is acceptable to the U.S. as long as it serves as the “policeman” in the Horn of Africa. We do not believe that you want generations of Ethiopians to remember you as the leader of the “free world” who gave a stamp of approval to a dictatorship that maims , murders, jails and forces to flee all those who stand for freedom, justice, the rule of law and democracy and is unrepentant in compromising Ethiopia’s sovereignty and territorial integrity.

Mr. President,

Equally, SHENGO shares views expressed by Jeffrey Smith of the Robert Kennedy Center for Justice and Human Rights who said, “The decision by President Obama to travel to Ethiopia, which has seen three opposition party members murdered this week alone, is very troubling and inconsistent with American values of respect for human rights, civil society, political pluralism and democracy.” We should like to add that over the past few weeks alone the ruling party has hunted down and jailed 45 leaders and members of the All Ethiopian Unity Party (AEUP) and is said to have murdered an unknown number of political and human rights activists. Accordingly, your visit to Ethiopia sends the wrong signal that the Government of the United States chooses to stand more firmly on the side of African dictators rather than on the side of those who advance

freedom, respect for human and civil rights, the rule of law and ultimately democracy. In the long run, only the emergence of a just, all inclusive, democratic and prosperous Ethiopia will serve as a beacon of stability, unity in diversity, Anti-terrorism and a symbol of good governance in the Horn of Africa. Sadly, your visit reinforces the perception among the vast majority of Ethiopia’s 100 million citizens that their quest for freedom, respect for human rights, national sovereignty, inclusion and genuine democracy is secondary to America’s short-term interests of fighting against and containing terrorism. This is the reason why we urge you to reconsider your visit. If your visit takes place as proposed, there is very little doubt that the Ethiopia’s Orwellian, Surveillance and corrupt State--that spies on its citizens at home and abroad using a 5 to 1 spy network---will assume the visit as a vindication and endorsement of legitimacy and use this as a license to repress and punish with impunity.

Mr. President,

In April this year, our organization joined renowned Human Rights organizations, Ethiopian- Americans and others and expressed our outrage concerning wrongful utterances and declarations conveyed by Under Secretary of State for Political Affairs Wendy Sherman who gave a stamp of approval to one of the most oppressive governments on the planet during an official visit to Addis Ababa, April 16, 2015. Her statement that “Ethiopia is a democracy that is moving forward in an election that we expect to be free, fair, credible, open and inclusive in ways that Ethiopia has moved forward in strengthening its democracy” is utterly baseless, untrue, demeaning to Ethiopians and harmful to America’s long-term interests. As we predicted, the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), the minority ethnic group that dominates the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) and in power since 1991, run against itself and declared that it won 442 of 547 Parliamentary seats in a cycle of sham elections boycotted by 30 opposition parties and deliberate dismantlement of others. We have no doubt the remaining seats whose strategic purpose is to appease the donor and diplomatic community will be allocated on the basis of ethnic and party loyalty.

In response to Ms. Sherman’s incredible statements, human rights groups such as Amnesty International, U.S.A, and the Committee to Protect Journalists (CPJ), Freedom House, Human Rights Watch, Freedom Now, Ethiopian Human Rights Project and International Rivers co- signed and sent a letter to Secretary of State John Kerry on April 17, 2015. “We are deeply troubled over the comments made by Under Secretary Wendy Sherman yesterday in Addis Ababa. The Under Secretary’s unfortunate statement calling Ethiopia a democracy puts the United States government on record as endorsing a government that systematically suppresses the fundamental rights of its citizens. Political pluralism and the ability of Ethiopians to freely express themselves, associate, and participate in peaceful assembly is far more restricted today than ten years ago under the same government, reflecting a dramatic deterioration in the government’s respect for fundamental civil and political rights. Since 2005, the ruling party’s dominance of the political landscape, repression of political opposition parties and restrictions on media and civil society have only increased.   Under Secretary Sherman’s comments are baffling to any observer of developments in Ethiopia and contradict the assessments of human rights organizations and even other governments. Her statements also undermine the courageous work of those pushing for a freer Ethiopia, many of whom are now imprisoned for exercising their fundamental human rights.” Your visit reinforces the perception that human rights, the rule of law and democracy are secondary in the execution of America’s foreign policy not only in Ethiopia but also the rest of Africa. At the same time, we take your word that you are committed to free and independent media and to the critical role of civil society in building democratic institutions. Allow us to flag the fact that the Ethiopian government is committed to a rigid and defiant policy that, regardless of global outcry, free and independent media and civil society won’t happen under its watch. This places your leadership in an awkward position.

On April 21, 2015, CPJ reported that “Eritrea and Ethiopia are the most censored nations in the world.” Last year, CPJ reported “A state crackdown on independent publications and bloggers in Ethiopia this year more than doubled the number of journalists imprisoned to 17, from seven the previous year, and prompted several journalists to flee into exile.” In 2014, the U.S. Department of State reported that Ethiopia is a source and destination for men, women and children “subjected to forced labor and sex trafficking.” Ethiopian girls as young as 8 years of age are subjected to “domestic servitude throughout the Middle East, as well as in the Sudan and South Sudan.” This and other reports indicate that “The central market in Addis Ababa is home to the largest collection of brothels in Africa.”

Mr. President,

You will agree with us that no country will prosper if its youth is subjected to repression and oppression, to lack of opportunities at home and to under-reported instability. The vast majority of Ethiopians, many born after the current government took power in 1991, are robbed of their dignity in two ways: they are not free to demand justice or to find employment at home; and they face uncertain and degrading conditions when they leave their homes in search of opportunities abroad. The beheading and wholesale massacre of 30 Ethiopian Christians by ISIS/Libya because of their faith and nationality attests to debilitating poverty and repression at home. Petrol bombing of Ethiopians and other killings in South Africa reinforce the primary reason why they are compelled to leave Ethiopia in the first place. According to Yemeni government sources and the International Organization for Migration (IOM) one million Ethiopian refugees are trapped in war torn Yemen. Many have been killed and a large number have been wounded. In November 2013, the Government of Saudi Arabia expelled 163,000 Ethiopians. Clearly huge aid has done little and will do little to accommodate the needs of the poor. This is among the numerous bad governance reasons why millions of Ethiopians fear their leaders and question the legitimacy of their own government accusing it that it is hopelessly corrupt and does not defend their rights and denies them freedom, justice and opportunities. The government’s response to protests and dissent is to murder selectively, arrest, jail and evict citizens. As the Department of State documents year after year, the Ethiopian government considers any peaceful dissent, criticism of the government and protest for justice and accountability, the rule of law and democracy as a form of “terrorism.” Ethiopia has one of the highest populations of political prisoners in the world.

Mr. President,

Ethiopians “are shackled by debilitating poverty “and mal-distribution of incomes and wealth as well as by draconian laws that keep them trapped. There is no single independent institution left to speak on their behalf. In “Journalism is not a crime” January 22, 2015, Human Rights Watch had reported as follows. “The Ethiopian government’s systematic repression of independent media has created a bleak landscape for free expression ahead of the May 2015 general elections. In the past year, six privately owned publications closed after government harassment; at least 22 journalists, bloggers and publishers were criminally charged, and more than 30 journalists fled the country in fear of being arrested under repressive laws.” This is the reason why independent media and civil society did not play any role in the May elections. Large amounts of money from aid, remittances and export earnings are stolen and taken out of the country each year; and there is no single institution to expose the bleeding. You will agree with us that sustainable and equitable development will not be attainable if the bleeding from corruption and illicit outflow continues and if political reform does not take place soon.

The U.S. Department of State “criticized the Ethiopian high court’s decision in January this year to proceed with the trial of journalists and Bloggers saying that it “undermines a free and open media environment.” Their case illustrates the enormous hurdles the new generation of Ethiopians face in demanding respect for their rights and freedoms that the U.S. and other Western democracies say are essential in lifting people out of poverty and oppression. The Ethiopian government continues to refuse to practice provisions of human rights contained in its own constitution. “Ethiopia is a multi-party democracy on paper” only. Having “won 100 percent of the votes” again, the ruling party will dominate parliament for the next five years. The façade of “free, fair and credible” last May did absolutely nothing to change single party preponderance and to move the country towards genuine democracy.

Mr. President,

You had said over and over again during your visits to Africa, North Africa and Asia that the United States is committed to the fundamental principle that advancement of human freedom enshrined in the rule of law is critical for durable peace, stability, sustainable and equitable development; and that free, independent and prosperous people are more likely to defend themselves and their countries against terrorism than people who are oppressed and marginalized by their own governments. We agree with these principles. However, Ethiopia’s federal police and judicial system is heavily politicized. The party and its endowments, a selected few individuals and the state dominate the national economy. The World Economic Forum rated Ethiopia 2.7 out of “a best possible score of 7” of its judicial system. This rating converges with other low scores including Freedom House’s latest rating of Ethiopia as among the “least free in the world.” The Ethiopian government dismisses these ratings as unacceptable. “The Ethiopian government has rejected criticism from Western governments, including the Department of State and human rights groups about the handling of the Bloggers” and other cases including massive displacements of indigenous people from their ancestral lands. We feel strongly that exclusion on the basis of ethnicity, religion and political affiliation and massive displacement of citizens from their lands contribute to instability, civil unrest and terrorism. Criminalization of independent media and civil society is detrimental to Ethiopia’s democratization. The crowding out of Ethiopia’s nascent private sector diminishes productivity and increased  employment. These are real.

Mr. President,

Close to your heart, we feel deeply that the criminalization of freedom of the press, civil society and political pluralism is against the long-term interests of the Ethiopian and American people and should not be given a stamp of approval for short term gains. Our organization reiterates in the strongest terms possible that it recognizes, acknowledges and supports the notion that terrorism in the Horn of Africa poses an existential threat to countries in the region, the U.S. and the World; and should be stopped.  We respectfully disagree that the way to deter terrorism is by a governing elite and state machinery that is bolstered by massive foreign aid to terrorize innocent people. It is tragic for us to witness this unexpected and dangerous convergence between a self-serving ethnic elite and globalization.

Mr. President,

As a President who cares deeply about the wellbeing of young people, especially girls, we wish to flag to you the plight of young people who face a dim future in their country and continue to leave in droves. This condition is facilitated by degrading human trafficking enterprises with government license and by illegal traffickers that sustain unprecedented level of human exodus of young girls and boys who leave Ethiopia at a rate unheard of in the country’s history. The Ethiopian government estimates that each day 1,500 young Ethiopians leave the country legally and another 3,500 through human smuggling. The mathematics of this many young people fleeing from Ethiopia depicts poor, exclusionary and oppressive governance. Clearly,  the benefits of Ethiopia’s growth have not been distributed fairly and justly. We can tell you with full confidence that Ethiopia’s youth see no hope in their own country’s future where a few elites at the top amass incomes and wealth that is best described as shameful and slanderous. The government of Ethiopia has done practically nothing to address this social crisis. By comparison, all countries that are genuine democracies make every effort to meet the aspirations and hopes of their people. They create jobs and other opportunities so that the country does not hemorrhage from the loss of its human capital. Don’t you agree with us that Ethiopia’s youth deserve to know your views and America’s commitment to sustainable and equitable growth whose social anchor are Ethiopia’s citizens, especially its youth?

Mr. President,

SHENGO wishes to highlight the fundamental and enduring principle that relations between the American and Ethiopian people span more than 100 years; and will endure for hundreds of years regardless of regime change. Accordingly, we urge you as leader and the government of the United States to stand firm on the side of the Ethiopian people by being more forthcoming on the need to respect freedom and human rights, justice, equality, the rule of law and democracy for all of the Ethiopian people. We feel strongly that America’s enduring contribution to Ethiopia and the rest of Africa is not to give aid that is most often stolen or wasted or to support and bankroll self-serving elites and dictators who provide services for money and serve short term interests. Rather, it is to demonstrate unbridled commitment in promoting America’s core values of good governance, the rule of law, equitable access to social and economic opportunities, advancement of civil society, independent and free media and political pluralism. In this connection, we urge you to use America’s enormous leverage and consider the following specific areas of opportunity for reform and action by the Ethiopian government:

1.            Immediate release of political prisoners, journalists and Bloggers.

2.            Rescind the draconian Anti-Terrorism and CSO Proclamations and

3.            Condition future U.S. intelligence, military, humanitarian and development assistance to Ethiopian government commitment to respect human rights, political, civil and religious freedom and free and independent media, the rule of law and democratization.

We are confident that when free from repression and oppression by their own government, the people of Ethiopia will do all in their power to defend themselves against terrorism.

We thank you for your understanding and attention to this urgent matter. Respectfull

Taye Zegeye, PhD Chairperson

Hits: 1663

በዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ኮንፈረንስ ሊደረግ ነው

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ የኢትዮ ጵያ  ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ወጣቶች ንቅናቄና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች የጋራ ኮንፈረንስ በመጪው ሀምሌ  July 2 ዋሽንግተን ዲሲ ላይ እንደሚያደርጉ ታወቀ። ለዝርዝሩ ይህን ይጫኑ

 

Hits: 1112