የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

የጨቋኝና አምባገነን ስርዓት ማሻሪያው የተባበረ ትግል ነው

መጋቢት፪ቀን፳፻፭

March 11, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ( ሸንጎ) በአገራችን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሕወሓት/ኢሕአዴግ አምባገነን መንግሥት የሚያካሂደውን የኃይል አገዛዝ በመቃወም በአገር ውስጥ በይፋ የሚንቀሳቀሱ 23 የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ ለመታገል የሚያሰችላቸው መግባባት ላይ መድረሳቸውን በመግለጽ ባወጡት መግለጫ እጅግ የተደሰ ተመሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።

 

 

 

Hits: 1557

የሽንጎው ከፍተኛ የአመራር አካል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

 

ነሃሴ ፯ ቀን ፳፻፭

Aug 13, 2013

የኢትዮጰያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ከፍተኛ የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ቅዳሜ ነሃሴ 4 ቀን፣ 2005 (Augest 10, 2013) በተሳካ ሁኔታ አካሄደ።

ይህ ስብሰባ የሽንጎው ሁለተኛ ጉባኤ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና የተለማቸውን የትግል አቅጣጫዎችበሀገር ውስጥና በውጭ  ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሰችሉ የተግባር  መመሪያዎችየሰጠ ሲሆን ይህንንም እውን ለማድረግ አስፈላጊ የሆ ኑ ኮሚቴዎችን መስርቷል፣የሰው ሀይልም መድቧል።

ምክር ቤቱ  በሀገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመመርመር ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ በተከታታይ ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ ህዝብን የማሸበር ተግባሩን በመቀጠል፣ በኢትዮጵያውያን ሰሊሞች ላይ በኢድ አል ፈጥርያካሄደውን ድብደባና ማንገላታትበታላቅ ሀዘን ተገንዝቧልድርጊቱንም በጥብቅአውግዟል።

በሰላማዊ መንገድ መሰረታዊ የእምት ነጻነት እንዲከበርና መንግስትም በሃማኖት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆምየታሰሩ የሀይማኖት መሪዎችም እንዲፈቱ የቀረበን ሰላማጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ስሊሙን ማህብረሰብ በጀምላበሽብርተኛና  አክራሪነት  የመወዘመቻ መቀጠሉእጅግ ሀላፊነት የጎደልውና አደገኛ እርምጃእንደሆነ በመገንዘብ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ከዚህ አይነት እኩይተግባሩ ተቆጥቦ ለሙስሊሙ ማህብረሰብ ያቄዎቸኳምላሽ እንዲሰጥ አሳሰቧል። ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር ያለውን የትግል አንድነት በድጋሜ ገልጿል።

የህወሓት/ኢህአዴግ የውስጥ ፍጥጫ፣ ዴሞክራሲን አይወልድም

የካቲት፳፮፣  ፪ሺ፭        

March 3, 2013

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ) በአገራችን ውስጥ ተንሰራፍቶ ያለው አምባገነን አገዛዝ ሕዝባችንን ከዕለት ወደ ዕለት  ለከፋ ስቃይ እየዳረገው እንደሆነ በተደጋጋሚ አስገንዝቧል።  አሁን ደግሞ አምባገነኑ አገዛዝ እራሱ ሊወጣ ወደ ማይችልበት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እየተዘፈቀ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል። የመለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ በህወሓት/ ኢህአዴግ ውስጥ የሚታየው ግልፅ ሽኩቻና ፍትጊያ እጅግ እየተፋጠነ መሄዱ ይህንኑ ሃቅ ያረጋግጣል።

 

Hits: 1371

የህወሓት/ኢህአዴግን አሸባሪ አገዛዝ በጋራ እንታገል

የካቲት 2፣ 2005   

Feb 9, 2013

 

ባለፉት ጥቂት ቀናት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በቁጥጥሩ ሥር የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎቶችን  በመጠቀም፣ በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎችን የሚወነጅል ሠፊ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ይህ “ጀሀዳዊ አራካት” በሚል ርዕስ በተደጋጋሚ በመሰራጨት ላይ ያለው  ፊልም፣  የሙስሊሙ ማህበረተሰብ የሀይማኖቱን አስተዳደር በተመለከተ ወክለው እንዲናገሩለት የመረጣቸው መሪዎቹ በእስር ላይ እያሉና ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት ተብየው እየታየ እያለ፣  እነዚህን በህዝብ የተመረጡ መሪዎች“እሰላማዊ መንግሥት ለመፍጠርና ሁከት ለማካሄድ የሚፈልጉ አሽባሪዎች”እንደሆኑበማሰመስል  በጥፋተኛነት የሚወነጅል ነው።

 

Hits: 1506