የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

ሰላማዊ የመብት ጥያቄ በሠለጠነ ውይይት እንጂ በአፈናና ግድያ መቼም ቢሆን አይፈታም

ኅምሌ 27 ቀን 2005 ዓ/ም

22 ዓመት ሙሉ ነፍጡን ከፊት አስቀድሞ የተፈጥሮ፣ ዴሞከራሲያዊና ሕጋዊ የሆኑመብቶቹንለማሰከበር በግምባር ሲታገል የቆየውን ምስኪን ህዝብ በገፍ እያሠረ፤ ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ እያሠቃየውና ግፍ በተሞላበት ግድያም እየቀጣው የቆየው የህወሓት/ኢሕአዴግ ግፈኛ አገዛዝ፣ይኸው ዛሬም በሰላማዊው ሕዝብ ላይ ባፈናና ግድያው ቀጥሎበት ይገኛል። 

ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ/ም በምዕራብ አሩሲና በሻሸመኔ አካባቢ ኢማሞቻችን/መሪዎቻችን ይፈቱ እያሉ በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ባሰሙ ሙስሊምኢትዮጵያውያንላይ የግፍ ግድያ መፈጸሙን ሽንጎው የተገነዘበውበከፍተኛ ሃዘን ነው። ልጆቻችሁ፣ አባቶቻችሁ፤ እናቶቻችሁ፣ እህቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ለህወሓት/ኢሕአዴግ ጥይት ሰለባ ለሆኑባችሁወገኖች ሁሉ ጽናቱንና ቁርጠኝነቱን ይስጣችሁ እያልን፤ ዛሬም እንደትናንቱ የታፈነ ድምጻችሁን በማስተጋባትና ጥያቄያችሁም ፍትሃዊ ምላሸ እንዲያገኝ ከጎናችሁ በመቆም ለመታገል ቃል እንገባላችሁዋለን።     ...........

Hits: 2113

በሽዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች ይሆናል!

June 2,2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) በዛሬው እለት  በሰማያዊ ፓርቲ ጠሪነትና በተለያዩ ድርጅቶች ተባባሪነት በአዲስ አበባ ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ያለውን አድናቆትና የትግል አጋርነት በድጋሜ ይገልጣል። ይህ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችጎ ዕድሜ፣ ጾታና እምነት ሳይነጥላቸው በአንድ ሆነው የሀገራችንን ህብር በሚያንጸባርቅና በታላቅ ሥነስርዓት የጋለ ስሜታቸውን በይፋ የገለጡበት ህዝባዊ ሠልፍ ፣ በሕዝባችን ላይ የተጫነው የፍርሀት ድባብ እየተሰበረ መምጣቱን የሚያመለከት ታላቅ እርምጃ ነው።   

 

 

Hits: 1495

ሕዝባችን ብሶቱን በሰልፍ ጭምር ለመግለጥ መነሳሳቱን እንደግፋለን!

ግንቦት3፣2005

ሕወሓት/ኢሕአዴግ አገራችን ላይ የጫነው በአንድ ጠባብ ቡድን የበላይነትና ዘረኝነት ላይ የተመሰረተው አገዛዝ የሕዝባችንን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማፈን  ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥፋት ላለፉት ሁለት ዓሥርትዓመታት ሲያካሂድ መቆየቱ ማንኛውንም ለዕውነትና ለፍትህ የቆመን ዜጋ ሁሉ ያሳዘነ ነው።

 

 

Hits: 1474

የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች መሆናቸው ያብቃ!

(May 3፣ 2013)

አቶ እሰክንድር ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ በሽብርተኛነት የፈጠራ ክስ ውንጀላ በረጅም እሰራት የሚማቅቁትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በቀጣይነት ለማሰቃየት በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰደውን እርምጃ  የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣በጥብቅ ያወግዛል።

 

 

Hits: 1330

አማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው

March 31, 2005

 

ህወሓት/ኢህአዴግ በህዛባችን ላይ የጫነው የጎሳ ፖለቲካ አስከፊ ገጽታው ላለፉት 22 ዓመታት በግልፅ እየሰፋ መጥታል።ያንዱንቋንቃ ተናጋሪ ከሌላው ጋር፣  የአንዱ አካባቢ ነዋሪ ከሌላው ጋር በአይነ ቁራኛና በአጥፊና ጠፊነት እንዲተያይ ተደርጓል።በዚህም የተነሳ የጎሳ ግጭት እጅግ ተስፋፍቷል። የህዝብ ህይወትና ንብረትም በሰፊው ጠፍቷል።የዜጎች የተረጋጋ ህይወት ተናግቷል።ይህ አጥፊ ፖሊሲም በአስቸኳይ  ካልተገታ ቀጣይና ምሰቅልቅል ቀውሰን እንደሚወልድ ግልጽ ሲሆን የዚህንም ቀውስ መጨረሻ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት እጅግ ይዘገንናል።

 

 

Hits: 1843