የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

በሳዑዲ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ የሚደረገውን ግፍ ለማስቋም በጋራ እንቁም

ህዳር ፫ ቀን ፳፻፮

November 11, 2013

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ከፍተኛ የአመራር ምክርቤትቅዳሜ ጥቅምት 29፣ 2006 ባደረገው ስብሰባ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሀገሪቱመንግስት የጸጥታ ሀይሎችእየደረሰ ያለውን ህገወጥ እስራት፣ድብደባና ስቃይ በታላቅ ሀዘንና አንክሮ አጢኗል። ለዚህ ግፍ ሰለባዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን እየገለጠ ከጎናቸው እንደሚቆምምአረጋግጧል።

ምክርቤቱ ይህ ህገ ወጥ ተግባር ባሰቸኳይ እንዲቆም ለማድረግ አለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ዘመቻ እንዲካሄድ የወሰነ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የሸንጎው አባላትና ደጋፊዎች ሰላማዊ ስልፍ እንዲያስተባብሩና እንዲያካሂዱ፣ስልፍ ለማካሄድ የማስተባበር ስራ በተጀመረባቸውቦታዎችም ከሌሎች ጋር በመተጋገዝ የሳዑዲ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚያካሂዱትንህገወጥ ተግባር ባስቸኳይ እንዲያቆሙግፊት እንዲያደርጉ፤ከሳዑዲ መንግስት ዲፕሎማቶችጋር  በግንባር በመነጋገር የኢትዮጽያውያን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የታሰሩት ባስቸኳይ እንዲፈቱና የተገደሉና ስቃይ የደረሰባቸውንም በተመለከተ አስፈላጊው ማጣራትና  ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በጥብቅ እንዲጠብቁአስቸካይ መመሪያ ስጥቷል።

በተጨማሪም፣ የሽንጎው አባል ድርጅቶችና ደጋፊዎችበሚገኙበት ቦታ ሁሉ ይህንኑ ጉዳይ አጽንዖት ሰጥተው  ለዓለምአቀፉ የመብት ተሟጋቾችና መንግሥታትበማስታወቅ በሳዑዲ መንግሥት ላይ የየራሳቸውን ግፊት እንዲያደርጉእንዲጠይቁ ተጨማሪ መመሪያ ሰጥቷል።    

በወገኖቻችን ላይ ሳዑዲ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ግፍ ለማስቆም ሁላችንም የፖለቲካ ልዩነትን ወደጎን አድርገን ባስቸኳይ እንድንተባበር  የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ጥሪውን ያቀርባለን።

ለወገን አድኑ ጥሪ በጋራ እንቁም፡

Hits: 2380

ትግሉ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ምሽጋችንም ደጀኑም የኢትዮጵያ ህዝብ ነው

 

መስከረም፳፪ቀን፳፻፭ ዓ.ም.

Oct 2,  2013

 

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ በመሠረታዊ ሰነዶቹ ላይ በግልጥ እንዳሰፈረው ለምሥረታው ዋና ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ በዋናነት ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተገፈፉባት፣ ዜጎች በእኩል የማይታዩባት፣ በዘርና በጎሳ እንዲከፋፈሉ የተደረገባትና አንድነቷን አደጋ ላይ የሚጥል አምባገነን ሥርዓት የተንሰራፋባት መሆኗን በማጤን፣ ይህንን አፋኝና አምባገነናዊ ሥርዓት አስወግዶ በህገ-መንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት የተባበረ ትግል እንደሚያስፈልግ በማመን ነው።

Hits: 2330

የግፍ አገዛዝ እንዲያከትም፣ ህዝብን ማአከል ያደረገው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥል!!

 

መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.

September 29, 2013

በዛሬው ዕለት በአዲስ  አበባ ውሰጥ የታየውን ታላቅ ሰላማዊ ትእይንተ ህዝብ በአመርቂ ሁኔታ ላሰተባበሩትና ለውጤት ላበቁት አንድነት ፓርቲንና የ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብን “እንኳን ደስ አላችሁ” እያልን የትግል አጋርነታችንንም እንገልጻለን።

እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ገዥው ክፍል የሰልፍ ቦታ በመከልከል፣ ለስልፉ በመቀስቀስና በማስተባበር ተግባር ላይ የተሰማሩትን በማዋከብ፣ በማሰር፣ ወዘተ....ይህ ሰላማዊ ሰልፍ እውን እንዳይሆን ቢሞክርም፣ በብዙሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ  ነዋሪዎች የፍራቻ ድባብን ሰባብረው፣  ለመብታቸው መከበር ቆርጠው መነሳታቸውን በዚህ ሰላማዊ ትእይንተ ህዝብ ላይ በመሳተፍ አሳይተዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫ

Hits: 1801

ሸንጎ በአዲስ አበባ የተጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ ይደግፋል

ጳጉሜ ፪፣ ፪፼፭

September 7, 2013

 

ህገመንግስታዊና  ተፈጥሮአዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ለማድረግ የሚጥሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ህወሓት/ኢህአዴግ ቀንተቀን እያጠበበው ከመጣው የፖለቲካ ምህዳር ሊያስወጣቸው የሚያደርገውን ጥረት ሸንጎ  እያወገዘ፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች  የሚደርስባቸውን አስከፊ እንግልትና በደል ተቋቁመው ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ማስቀጠላቸውን  ያደንቃል።

ያለውን አምባገነን አገዛዝ ታግሎ ዴሞክራሲያዊ  ስርዓትን ለመፍጠር የታጋይ ድርጅቶችን አንድ ላይ መቆም ግድ የሚል በመሆኑ በነጠላ የሚደረጉ ትግሎችን በማስተባበር ትግሉን ውጤታማ ማድረግ ወደሚቻልበት ደረጃ ማድረስ አስፈላጊ ነው። አንድነት መስከረም አምስት በአዲስ አበባ የጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ  33ቱ  ፓርቲዎች በጋራ ለማዘጋጀት መወሰናቸው እሰየው የሚያሰኝና ትግሉ ጥሩ አቅጣጫ ይዞ መጓዝ እንደጀመረ የሚያመላክት ነው። ይህም ትብብር ከፍወዳለ ደረጃ እንደሚደርስ ትስፋችን ነው።

የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲህ ተባብረው በሚቆሙበት ወቅት ህዝቡም በነቂስ በመውጣት የተባበረ ጠንካራ ጉልበት እንዲፈጥር  ሸንጎው ያሳስባል።

በተባበረ ትግል ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንገነባለን!

Hits: 1924

ዓባይን መገደብማ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕልም ነው

በስተሰሞኑ ዓባይን አስመልክቶ ህወሓት/ኢህአዴግ በተለመደ ፕሮፖጋንዳው የራሱን ‘አገር ወዳድ ሚና’ በማጉላት ተቃዋሚውን አኮስሶ ለማሳየት የሚያደርገው ጥረት እየተንፀባረቀ ነው።  በዓባይ ግድብ ዙሪያም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች የህወሓት/ኢህአዴግ የመገናኛ ብዙሃን መሣሪያዎችና ተባባሪዎቻቸው የሚያናፍሱትን  ፕሮፖጋንዳ ሕዝባችን ማዳመጥ ካቆመ ሰንብቷል።  ይሁንና በዓባይና በግድቡ ጥያቄ ላይ ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ሸንጎው አቋሙን ግልጽ ማድረጉ ደግሞ ተገቢ ነው።  ስለዚህ በመጀመሪያ ሸንጎው በግድቡ መሠራት ላይ ያለውን አቋም (ህወሓት/ኢህአዴግም የዓባይ ግድብን ራዕይ ብቸኛ አፍላቂ ናባለቤት ነኝ ባይነትና በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በተቃዋሚው  ላይ  የሚያካሂደው አሉታዊ ቅስቀሳ በተመለከተ እውነታውን ሲያመላክት) ቀጥሎም ሀገራችን ኢትዮጵያ ወንዙን  የመጠቀም መብቷን በተመለከተ ግብፅ በሰነዘረችው ማስፈራሪያ ላይ ሸንጎ ያለውን አቋም ያቀርባል።.......

Hits: 1497