የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

Switch to desktop Register Login

Home

የመብት ማስከበር ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል

 

የስርአቱ ጸጥታ ሀይሎችና ባለስላጣኖች ባለፈው እሁድ ሰኔ 26፣ 2016 ሰማያዊ ፓርቲ  በባህርዳር ለማካሄድ ያቀደውን ህዝባዊ ስበሰባ በመከልከል ለዚሁ ስራ ተሰማርተው የነበሩትን የፓርቲው የህግ ክፍል ሀላፊና የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አዲሱ ጌታነህ፣ ሌሎች የድርጅቱን አባላትና የባህር ዳር አደራጆችን እንዲሁም ለዚሁ ስራ የሚያገለግለውን መኪና ሺፌርረዳት  ሳይቀር  ባጠቃላይ አስራአንድ ሰዋች በማሰር የታቀደው የህዝብ ስብሰባ እንዳይሳካ አድርጓል።..........ሙሉውን አስነብበኝ

Hits: 2071

የመብት ረገጣውንና የከፋፋዮችን ሤራ በጋራ እናስወግድ!

በሀገራችን ውስጥ ሀሳቡን በነፃ ለመግለጽ የሚሞክር ሁሉ ከገዥው ቡድን የሚሰጠው ምላሽ የሚያነሳውን ጥያቄ በመመርመር፣ የደረሰበትን ብሶት በማዳመጥ ሰላማዊ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ ድብደባ፣ እሥራት፣ ስቃይና ግድያ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ይህ ለሃያ ሦስት ዓመታት ሳያባራ የቀጠለው የግፍ ተግባር እነሆ በቅርቡ በአምቦ፤ በነቀምት፤ በጊምቢና በሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች ውስጥ በዘግናኝ መልኩ ተደግሟል። ጨካኙ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዛ በሥርዓቱ ፖሊሲ ላይ ተቃውሟቸውን ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱ ተማሪዎችን፣ ከአሁን በፊት በጎንደር፣ በአዋሳ፣ በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች እንዳደረገው፣ ዛሬም በጥይት ደብድቦ ብዙዎችን ገድሏል፤ ሌሎችንም አቁስሏል። ....... ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

Hits: 1713

የሸንጎ አመራር ምክርቤት ጠቅላላ ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

የሸንጎው ከፍተኛ አመራር ምክር ቤት ስብሰባ የህዝቡን ትግል ለማጠናከር የሚያሰቸሉ ተጨማሪ ውሳኔወችን በማስለላለፍ ተጠናቀቀ

ህዳር 10፣ 2007 ( ኖቨምበር 19፣ 2014)

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ  (ሽንጎ)  ከፍተኛ የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን  ቅዳሜ  ሕዳር 6፣ 2007 ( ኖቨምበር 15፣ 2014) በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል።

በዚህ ስብሰባ የህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ እያካሄደ ያለቸውን አሰቃቂና ሀላፊነት የጎደለው ተግባሮች በዝርዝር በመመርመር ይህ የግፍ ስርዓት ተወግዶ አንድነቷ በተረጋገጠ ኢትዮጵያ  የሁሉም ዜጎች ሙሉ ዴሞክራሲያዊ መብት ተከብሮና የህግ የበላይነት ሰፍኖ ለመኖር የሚያስችል ህገመንግስታዊ ስርአትን እውን ለማድረግ የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዞ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቷል።......ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

Hits: 1347

የሽንጎው ከፍተኛ የአመራር አካል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

 

ነሃሴ ፯ ቀን ፳፻፭

Aug 13, 2013

የኢትዮጰያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ከፍተኛ የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ቅዳሜ ነሃሴ 4 ቀን፣ 2005 (Augest 10, 2013) በተሳካ ሁኔታ አካሄደ።

ይህ ስብሰባ የሽንጎው ሁለተኛ ጉባኤ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና የተለማቸውን የትግል አቅጣጫዎችበሀገር ውስጥና በውጭ  ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሰችሉ የተግባር  መመሪያዎችየሰጠ ሲሆን ይህንንም እውን ለማድረግ አስፈላጊ የሆ ኑ ኮሚቴዎችን መስርቷል፣የሰው ሀይልም መድቧል።

ምክር ቤቱ  በሀገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመመርመር ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ በተከታታይ ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ ህዝብን የማሸበር ተግባሩን በመቀጠል፣ በኢትዮጵያውያን ሰሊሞች ላይ በኢድ አል ፈጥርያካሄደውን ድብደባና ማንገላታትበታላቅ ሀዘን ተገንዝቧልድርጊቱንም በጥብቅአውግዟል።

በሰላማዊ መንገድ መሰረታዊ የእምት ነጻነት እንዲከበርና መንግስትም በሃማኖት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆምየታሰሩ የሀይማኖት መሪዎችም እንዲፈቱ የቀረበን ሰላማጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ስሊሙን ማህብረሰብ በጀምላበሽብርተኛና  አክራሪነት  የመወዘመቻ መቀጠሉእጅግ ሀላፊነት የጎደልውና አደገኛ እርምጃእንደሆነ በመገንዘብ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ከዚህ አይነት እኩይተግባሩ ተቆጥቦ ለሙስሊሙ ማህብረሰብ ያቄዎቸኳምላሽ እንዲሰጥ አሳሰቧል። ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር ያለውን የትግል አንድነት በድጋሜ ገልጿል።

የተቃዋሚዎች ኅብረት የድል ዋስትና ነው

ባለፉት ጥቂት ቀናትና ሳምንታት በሀገራችን ውስጥ የታየው ሁኔታ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ አሁንም አስከፊ ብትሩን ከማሳረፍ ከቶውንም ወደኋላ እንደማይልነው።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊ የሆኑ በርካታ ወጣት ሴቶች ወገኖቻችን ስለ መብ መከበር መፈክር አሰምተዋል በሚል ሰበብ ለእስር እንደተዳረጉ ተመልክተናል። ዓርብ መጋቢት 12 (March21,2014) ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ እንዳይችሉ በገዥው ቡድን የፀጥታ ኃይሎች መታገዳቸውን አስተውለናል።

             

 

Hits: 1590

External links are provided for reference purposes. Shengo is not responsible for the content of external Internet sites. Copyright © 2013 የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

Top Desktop version