የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

እዚያም ቤት እሳት አለ! በሻአቢያም ይሁን በህወሓት/ኢህአዴግ የሚካሄድ የመብት ረገጣ ሁላችንንም ሊያሳስብ ይገባል

በአንድ ከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ድንገት ሰፈራቸው በእሳት ጋይቶ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ፣ምናልባት ብንድን ብለው ወደሌላ አቅጣጫ ካለው ሰፈር ለመጠለል ሲሮጡ፣ ከዛኛውም ሰፈር እንደዚሁ እሳት ተነስቶ ኑሮ፣ ብዙ ሰዎች ወደዚህኛው ሰፈር ሲገሰግሱ መሃል ቦታ ላይ ተገናኙ። ከመካከላቸው አንዱ የእኛ ሰፈር በእሳት ጋይቶ ለመጠለል ወደ እናንተ ሰፈር እየመጣን እናንተ ደግሞ በእጥፍ ቁጥር ወደእኛ እየገሰገሳችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ የደረሰብንን ጉዳት ሰምታችሁ እሳቱን ለማጥፋት ነው ወይስ እኛን ከመንገድ ላይ ተቀብላችሁ ልታስተናግዱን ነው ይኸ ሁሉ ሰው የመጣው? ብሎ የወዲያኛውን ሰፈር ኗሪ ጠየቀ። የተጠየቀውም ሰው ግር ብሎት የእሳቱ መነሳት እንዴት ከእናንተ ጆሮ ደረሰ? ለማጥፋት ልትተባበሩን ነው የመጣችሁት? ብሎ በመገረም መልሶ ጠየቀው።
ሁሉም ግራ ተጋቡና የየራሳቸውን ሰፈር መቃጠል እያነሱ ሲጨቃጨቁ በመገረም የሚያስተውሉ አንዱ አረጋዊ ሰው፤ምነው ወገኖቼ ተደማመጡ እንጂ! ሁለታችሁም እኮ እሳት ያባረራችሁ የእሳት በደለኞች ናችሁ። እንዴት መደማመጥ ይሳናችዃል? አንዳችሁ የሌላውን መቃጠል መረዳት ተስኗችሁ የእኔ ሰፈር ነው የተቃጠለው፣ የአንተ ሰፈር ሰላምና ከእሳት ነጻ ነው፤ መባባል አመጣችሁ? አንዱ የአንዱን መቃጠል መቀበልና ማወቅ እንዴት ይሳነዋል? ሰው ወዶ ቤቱንና ሰፈሩን አይለቅም። እሁለታችሁም ሰፈር እሳት አለ፣የሁለታችሁም ቤት እየጋየ ነው።እሳት እሳት ነው። አንዱን አጥፍቶ ሌላውን አይምርም።እሳት አንዱን የሚያቃጥል ሌላውን የሚያበርድ አይደለም።በሁለታችንም ሰፈር የተነሳውን እሳት የለም ብሎ መካድ ከለኮሰው ጋር ተመሳጥሮ ጉዳትን አለማወቅና አለመቀበል ነው። እሳት ሁላችንንም እያጠፋ ቤት ንብረታችንን እያወደመ ነው። ይልቁንስ አንድ ላይ ሆነን የለኮሰውን እንፈልግና ለሕግ እናቅርብ፤ ለወደፊቱም እሳት እንዳይነሳ ማገዶ ከሚሆን እንጨት የተሻለ ቤት ለመስራትና ከአደጋው ለመገላገል መላ እንምታ በማለት በሳል አስተያየትና ምክር አቀረቡ።
እኛ ኢትዮጵያውያንና ቀደም ኢትዮጵያውያን የአሁኑ ኤርትራውያን ሕዝቦች በምንኖርበት አገር የሰፈኑት አምባገነን ስርዓቶች የሚፈጁ እሳቶች ናቸው። ሁላችንም የሚፈጽሙት ግፍና በደል ሰለባዎች ነን፡፤ሁላችንም በተመሳሳይ አምባገነንና ጸረ ዴሞክራሲያዊ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች በሆኑ፣ ተደጋጋፊ ስርዓቶች ውስጥ የምንማቅቅ፣ ለስደት የተዳረግን፣ አንድ አይነት ፍላጎት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ እምነት መልክ፣ ስም ስነልቦና ያለን ዜጎች ነን።
ሁለቱ አምባገነን ስርዓቶች በሚቆጣጠሩት መሬት ውስጥ ለሚኖረው ሕዝብ የሚያቃጥሉ እሳቶች ናቸው። የእነዚህን ስርዓቶች ክፋትና በሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን በደል መካድና እንደ በጎ አድራጊ መቁጠር፣ወይም አንዱን በማርከስ ሌላውን በማንገስ ወይም በማወደስ ፣የራስን በደል እያጎሉ የሌላውን ሕዝብ ስቃይ እንደሌለ መካድ በሰው ቁስል ላይ እንጨት እንደመክተት ይቆጠራል። ለማይረባ ጥቅም ሲሉ ሌላውን መሰል ሕዝብ አሳልፎ መስጠትና ችግሩን አለመገንዘብ በታሪክ ያስጠይቃል። ከጠላት የበሉት በሶ፣ ይወጣል ደም ጎርሶ እንደሚባለው ፣ሕዝብ ከጠላው ስርዓትና መሪ ጋር አብሮ መቆም ሲገረሰስ አብሮ መጨፍለቅ እንደሚሆን ማሰቡ ብልህነት ነው። ከአንድ ሕዝብ ከጠላው መሪና ስርዓት ጋር ከመሰለፍ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በደሉን ቢያውቁለት የተሻለና በድል ማግስት የሚያኮራ ይሆናል። ከማፈርና አንገት ከመድፋት ያድናል።
በተመሳሳይ ደረጃም ለጥቂት ጊዜአዊ ጥቅም ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህወሃት መራሹን አምባገነን ስርዓት ዴሞክራቲክ አድርጎ ማቅረብና በኤርትራ መሬት ላይ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመት በፈላጭ ቆራጭነት በስልጣን ላይ የተቀመጠውን የሻእብያ መንግሥትና መሪ ዴሞክራትና አርቆ አሳቢ፣ ለሕዝብ ተቆርቋሪ አድርጎ ማቅረብ የሚያስተዛዝብ ጉዳይ ነው።
እነዚህን የሕዝብ የመከራ ምንጭ የሆኑትን አምባገነን ስርዓቶች በህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ግፍ  መካድ፣ ብሎም ለነሱ ድጋፍ መስጠትና ያልሆኑትን ናቸው እያሉ መካብ የዓለም ሕዝብ የሚያውቀውን እውነት መካድ ማለት ነው።
ከኢትዮጵያና ከኤርትራ በየቀኑ በቀይባህርና በሜዲትራንያን ባሕር አደጋን ለመጋፈጥና ካሉበት ኑሮ የነጻነት ሞትን መርጠው የሚሰደዱትን እንደ ቅንጡ አገር ጎብኝ በመቁጠር ከአገራቸው የሚያባርራቸው ምክንያት የሆነ መንግሥትና ስርዓት የለም ብሎ ማቅረብ ነው።
በሁለቱም አምባገነኖች የሚረገጡት ሕዝቦች የጋራ ችግር አለባቸው፤ ያም የመልካም ስርዓት አለመኖርና  ቀና መሪ አለመኖር ነው። አለዚያማ እንዴት ሰው አገሩን፣ ወገኑንና ቤተሰቡን ጭምር ጥሎ ለመድረሱ ዋስትና በሌለው መንገድ ወደ ማያውቀው አገር ይሰደዳል?  ድህነት ነው ቢባልም፣ድህነቱ በምን ምክንያት ተፈጠረ ብሎ መጠየቅ ይገባል። ለዚያ ደግሞ መልሱ ከስርዓቱ ጋር የተያያዘ ሆኖ ይገኛል።
የኢትዮጵያና የአሁኗ ኤርትራ ሕዝብ አብሮ በአንድ አገር ልጅነት ለዘመናት ኖሯል፡፤ወደፊትም መልሶ ሊኖር ይችላል።በሕዝብ  የሚመረጥ፣ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ፣ሕዝብ የሚያቀራርብ ስርዓት እንዲሰፍን፣ አብሮ ለመኖር የሚያስችለውን ፍላጎት እንዲዳብር የሚሻ ዜጋ አሁን ከሕዝቡ ጎን ይቆማል እንጂ ከጨቋኝ ጋር አይሞዳሞድም። ለአምባገነኖች ድጋፍና እውቅናም ሰብሳቢም አሰባሳቢም  አይሆንም።
በሁለቱም ሕዝቦች ላይ የተጫኑትን ጨቋኝና አምባገነን አገዛዞች ለውጦ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመመስረት፣ በርግጥም የህዝብን ልዖላዊነት እውን ለማድረግ፣ በሁሉም በኩል ያሉ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች በጋራ በመቆምና በመተባበር የህዝብ ወገንተኛነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ) አመለካከት በኤርትራና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት ዜጎች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው፣በስልጣንም ላይ ያሉት አምባገነኖች እንደዚሁ።
ሁለቱም ሕዝብ በማራራቅና በማለያየት ስልጣን ላይ የተቀመጡት አምባገነኖች ዕድሜ ሲያጥር ካለፍላጎታቸው ተገደው የተለያዩት የሚቀራረቡበትና በሰላም የሚኖሩበት ዕድል ይፈጠራል ብሎ ያምናል።የሁሉንም ችግር ለመፍታት የሚያስችል ስርዓት እንዲመጣ በህብረት መታገል ተገቢ ነው ብሎ ያምናል እንጂ ለትንሽና ጊዜያዊ ጥቅም ሲል ህዝብን አሳልፎ አይሰጥም።
ህወሃትና ኢሕአዴግን የሚደግፉ ኤርትራውያንም ሆኑ ሻብያንና ኢሳያስን የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ማሰብ ከሚገባቸው ነገር ውስጥ አንዱ የህዝብ መሰረታዊ መብት መከበር ከጊዚያዊ የፖለቲካ ድግፍ ማሰባበብ ባለፈ ሁኔታ ሊታይ የሚገባው ክቡር ጉዳይ እንደሆነና በመንገዳገድ ላይ ያለው የነዚህ አምባገነኖች ስርዓት ሲወድቅ ምን ይደርስብኝ ይሆን? የእኔ ተግባር ሕዝብ ሊያራርቅ ወይም ሊያቀራረብ ይችላል ወይ?ብሎ መጠየቅና መንገዳቸውን
ማስተካከልና ማረም እንደሚኖርባቸው ነው።

በየቦታው ያሉ አምባገነኖች በህዝብ ጣምራ ትግል ይወገዳሉ!!
የአንዱ ጭቁን ሕዝብ በደል ለሌላው ጭቁን ሕዝብ በደሉ፣የአንዱ ጭቁን ሕዝብ ድልም ለሌላው ጭቁን ሕዝብ ድሉ ነው።

በአንድነት፣ለአንድነት!!!

Hits: 2053

Press Statement

 

Following the European Parliament’s Resolution of January 21, 2016 on the situation in Ethiopia “strongly condemning the recent use of excessive force in Oromia and in all Ethiopian regions,” Shengo expressed its appreciation to the EU and called upon the Congress of the United States to take a similar stand. In this regard, we recognize the concerted and relentless campaign made by Ethiopian civil society, political, spiritual and professional groups as well as individuals.

The United States Senate Resolution “supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance” in Ethiopia could not have come at a most opportune and critical time in Ethiopia’s long history. In particular, we note with appreciation that the Senate “condemns killings of peaceful protestors and excessive use of force by Ethiopian Security forces, the arrest and detention of journalists, students, activists and political leaders, and the abuse of the Anti-Terrorism Proclamation to stifle political and civil dissent and journalistic freedom.”

Shengo has been calling on the government of Ethiopia to release all political prisoners, desist from forcible evictions of indigenous people from their lands and repeal the draconian 2009 Anti-Terrorism and Charities and Societies Proclamations that have been used as blunt instruments to punish dissidents and to degrade civil society. We are encouraged by the Senate’s call on the government of Ethiopia to “refrain from violence (state, our emphasis), halt the use of excessive force by security forces and conduct a full, credible, and transparent investigation into killings that took place in Oromia, and hold security forces accountable for wrong doing through public proceedings, repeal proclamations that are used as political tools to harass or prohibit funding for civil society organizations.”

We are especially encouraged by the Senate’s “Call on the Secretary of State to conduct a review of security assistance to Ethiopia.” Ethiopian civic, political groups, academic and professional groups have questioned repeatedly the wisdom of providing American security assistance to a state and government that uses these tools to punish its own people with impunity. Equally, we are encouraged by the prospect that USAID “would advance democracy and governance” and apply due diligence and oversight in the provision of both humanitarian and development assistance. The government of Ethiopia continues to deny food and other forms of humanitarian assistance to potential dissidents and non-party members. It also restricts official development assistance on the basis of political and ethnic loyalty.

Last but not least, Shengo is enormously gratified by the resolution that the Senate “stands by the people of Ethiopia, and supports their peaceful efforts to increase democratic space.” Together, we have a golden opportunity to leverage the resolutions of the two most significant donors and diplomatic supporters to the Ethiopian regime.

Hits: 1737

ለሕዝብ ያልቆመ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት አይመክትም

የአንድ አገር ድንበር የሚደፈረው፣ ሕዝቡ ለተለያዩ ጥቃቶች የሚጋለጠው የአገሩን ድንበር፣ የሕዝቡን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና ሊሰጥ የሚችል በሕዝብ፣ ለሕዝብ፣ የሕዝብ የሆነ መንግሥት በሌለበትና ለጸረ ሕዝብ ሃይሎች አመቺ ሁኔታ ሲፈጠር ነው።

ለአለፉት ሃይ አምስት ዓመታት ሥልጣኑን በሃይል የጨበጠው የጎሳ ስብስብ በተደጋጋሚ የአገራችንንና የሕዝባችንን ጥቅምና ደህንነት ለአደጋ እያጋለጠ እራሱም የአደጋው ፈጣሪ እየሆነ መቆየቱን የሥልጣን ዘመን ታሪኩ ይመሰክራል።

የስልጣን ዕድሜውን ለማርዘም በሁከትና በሽብር፣ በብጥብጥና በእርስበርስ ቀውስ አንድ ጊዜ ቀስቃሽ ሌላ ጊዜ ወቃሽ፣ አንድ ጊዜ አዘጋጅ ሌላ ጊዜ አሶጋጅና አስታራቂ፣ እየሆነ በመቅረብ ለማምታታት ቢሞክርም በየቀኑ እውነተኛ ገጹና ባህሪው እየተጋለጠ ሕዝብን ማታለል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። .......... ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

Hits: 1562

ሀላፊነት እወስዳለሁና ይቅርታ እንጠይቃለን ማለት በተግባር መተርጎም አለበት

 

 

በ PDF ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርአም ደሳለኝ  ከጥቂት ቀናት በፊት ለፓርላማው ባቀረቡት ዘገባ ውስጥ ጨምረው በሀገራችን ባሁኑ ሰአት በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ጎልቶ የሚታየውን የህዝን መነሳሳት  ከመልካም አስተዳደር መጥፋትና  ከስርአቱ ብልሽት ጋር

የተያያዘ እንደሆነ   ለተፈጸመው በደል ተጠያቂ  እንደሆኑም  አምነው “ይቅርታ “ ጠይቀዋል።

እጅግ የዘገየ ቢሆንም ሀላፊነት እወስዳለሁ ፣ ለተሰራው ወንጀልም ተጠያቂ ነን ማለትና ይቅርታ መጠየቅ አበረታች ነው። ሆኖም ይሀ ተራ ቃል ብቻ እንዳይሆን በግልጽ በተግባር ሊታገዝ ይገባዋል።

ሁሉም እንደሚያውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተቀሰቀሰው የህዝብ መነሳሳት  ጋር  በተያያዘ ሰበብ ወደ እስር የተወረወሩ የፖለቲካ መሪወች ለምሳሌ አቶ በቀለ ገርባ እና በሽወች የሚቆጠሩ ዜጎች ይገኛሉ። በወልቃይትና ጠገዴም እንዲሁ ተመሳሳይ ሁኔታወች ተከስተዋል። ስህተተኛ ነን ካሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እነዚህን ያላግባብ ታሰረው የሚማቅቁ ወገኖቻችንን ሁሉ ባስቸኳይ ከእስር መፍታት ይጠበቅባቸዋል። የተፈጠረው  ስህተትና ቀውስ  ከራሱ ከስርአቱ ፖሊሲና አሰራር የመነጨ መሆኑን  ካመነ ፣ መሰረታዊ መብታቸውን በመግለጽ ላይ እያሉ የታሰሩ ሁሉ አሁኑኑ ከእስር መለቀቅ አለባቸው።ቀጣይ የመብት ረገጣውንም አሁኑኑ ማስቆም ያሰፈልጋል።

ደጋግመን እንዳልነው ሁሉ ከዚህም  በተጨማሪ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ህይወታቸው ለጠፋው ፣ ንብረታቸው ለወደመው ሁሉ አስፈላጊውን ካሳ መክፈል የግድ ይላል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ፍትህን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነውና የዚህን ወንጀል ሁኔታ  በነጻ የሚመረምር ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ አጣሪ አካል መስርቶ ያለአንዳች ጣልቃ ገብነት ተግባሩን እንዲያከናውን ውጤቱንም ባጭር ጊዜ በይፋ ለህዝብ እንዲያሳውቅ ማድረግ ትእዛዙን የሰጡም ሆኑ በስላማዊው ህዝብ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሁሉ በይፋ ለፍርድ ባስቸኻይ እንዲቀርቡ ማድረግ ያሰፋልጋል።

ይህ ሳይሆን “ይቅርታ ጠይቀናል፣ ሀላፊነት እንወስዳለን “ ወዘተ የሚሉ ቃላቶች ተራ ቃላት ብቻ ሆነው ይቀራሉ። ያለፉት 24 አመታት ከስርአቱ መሪወች ተመሳሳይ በተግባር ያልተደገፈ ንግግርን በተደጋጋሚ  እንደሰማን  የሚዘነጋ አይደለም።  ይህ ደግሞ የህዝባችንም ቁጣ ይበልጥ ያብሰዋል እንጂ  ሊያበርደው ከቶውንም አይችልም።

በመጨረሻም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ስርአቱ ለ24 አመታት እንዳደረገው በማፈን፣ በመግደል፣ በመከፋፈልና የህዝብን ጥያቄ በማስፈራሪያነት በመጠቀም  ለመቀጠል የማይችልበት ሁኔታ ላይ እንደደረሰና ሀገራችንም አስፈሪ ወደሆነ ቀውስ እንደተገፋች ተገንዝቦ ራስን ከማታለል ተላቆ የሀገሪቱን ችግሮች ሁሉን አቀፍ በሆነ በብሄራዊ መግባባትና በብሄራዊ እርቅ ለመፍታት ሳይዘገይ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ አለበት አንላላን። የሀገራችን ውስብስብ ችግሮች ባንድ ድርጅት ብቻ ሊፈታ እንደማይችል መገንዘብ የግድ ነው።

ለስርአቱ ቅርበት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ያለውን እውነታ በጊዜ ተገንዝባችሁ አደጋውን ለመቀነስና የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት ፍላጎት  ተግባራዊ ለማድረግ ከህዝብ ጎን እንድትሰለፉ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በተደጋጋሚ እንዳሳየነው ብሄራዊ መግባባትና እርቅ እንዲሁም  ሀላፊነት እወስዳለሁ ማለት ካንገት በላይ ሳይሆን ከልብ መሆን አለበት።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

Hits: 1829

የካቲት - የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነጻነቱ የታገለበትና መስዋዕት የከፈለበት ታሪካዊ ወር

የካቲት በኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታየያዘ ወር ነው። ጣሊያን አገራችንን በወረረበት ጊዜ ዜጎች በአንድ ቀን ጀንበር በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30ሺ ሰው በላይ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ብቻ በጠላት መትረየስ የታጨዱበት፣ በአካፋ የተጨፈጨፉበት መስዋእት በመሆን ደማቸውን ያፈሰሱበት ዕለት በመሆኑ ሊታሰብና ሊከበር ይገባዋል። በዚያን ዕለት ጣልያኖች እርምጃውን ሲወስዱ ሕዝብ ፈርቶ ያድርልናል፣ ይገዛልናል በሚል እምነት ነበር። ውጤቱ ግን የብዙ ወጣቶችን ልብ የቀሰቀሰና ለትግል እንዲሰለፉ ያደፋፈረ ሆነ።

በዚያ ዓይን ያወጣ የጭካኔ እርምጃ የተጨፈጨፉት ዜጎች ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተወለዱና ከልዩ ልዩ ያገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጣሊያን ወራሪ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ የሆነው ግራዚያኒ ሕዝቡን ሰብስቦበሱ የሚመራውን የወራሪውን አስተዳደር እንዲቀበልና ባወጣው ሕግ እንዲተዳደር ለማድረግ ብሎም የጣሊያን መንግስት ለኢትዮጵያ እድገትና መሻሻል እንጂ ለመጉዳት የመጣ አለመሆኑን ለማሳመንና ለድሆች እርዳታ እሰጣለሁ በሚል የማታለያ ሰበብ ስብሰባ ጠራ...... ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

Hits: 1316