የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

የህወሃት/ኢህአዴግን የእልቂት አዋጅና መሰናዶ ተባብረን አናክሽፍ

በህዝብ ተቃውሞና ትግል የተወጠረው የጎሰኞች ስብስብ የሆነው የህወህት/ኢህአዴግ አፋኝ አገዛዝ ከዓመት በፊት የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞና አመጽ ለማፈንና ብሎም ለማጥፋት የጊዜያዊ አዋጅ ማወጁ የሚታወቅ ነው። አዋጁና አዋጁን ተከትሎ በህዝቡ ላይ የሚወሰደው ግድያ፣ አፈና፣ እስራት...ወዘተ በደቡብና በመካከለኛው ያገሪቱ ክፍሎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ለጊዜው የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ የገታው ቢመስልም በአገሪቱ ሰሜናዊ ግዛቶች በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የህዝቡን ትግል ሊያዳፍነው ቀርቶ መቋቋም አልቻለም።  ስለሆነም ሌላ ተጨማሪ የእልቂት እርምጃ ለመውሰድ በይፋ በማወጅ ተንቀሳቅሷል።  ........ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

 

 

 

 
 

Hits: 610

የወልቃይት--ጠገዴ ጉዳይ ብሄርን መሰረት ያደረገ የክልሎች አሸናሸን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው

 የኢትዮጵያ  ህዝብ  የጋራ  ትግል  ሽንጎ  (ሽንጎ)  የስራ  አስኪሃጅ  ኮሚቴ  የሀገራችንን  ሁኔታ  በየጊዜው እየገመገመ የፖለቲካ አቅጣጫ ማሳየት አንዱ ተግባሩ ነው። የስራ አስኪሃጅ ኮሚቴዉ በቅርቡ ትኩረት የሰጠው አበይት ጉዳይ ዛሬ በሃገሪቱ ሰፍኖ ያለዉ፤ በህወሓትና አጋሮቹ ተቀነባብሮ ሕገ-መንግሥት የሆነው ብሔር-ተኮር  ፌደራሊዝም (Ethnic Federalism) ያስከተለዉን ሃገር  አቀፍ ምስቅልቅል በሰከነ አስተያየት መርምሮ ሊያስከትለው የሚችለውን አደጋ በግልጽና በማያሻማ ደረጃ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማቅረብና መፍትሄዎችን መጠቆም ነው። 
በህወሓቶች

  ........  ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

Hits: 569

ከድጡ ወደማጡ!!

 

ለህዝብ ደንታ የሌለውና የወዳጅ ምክር የማይቀበል መንግስት የመጨረሻ እጣ ፈንታው መወገድ ነው

ላለፉት ሃያስድስት ዓመታት በጉልበት ስልጣኑን ጨብጦ ያሻውን ሲያደርግ የኖረው የአምባገነን የዘረኞች ቡድን ከአሁን በዃላ እያጭበረበረና እየዋሸ፣እየገደለና እየዘረፈ የሚኖርበት ዘመኑ እየተመናመነ መምጣቱን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች ተከስተዋል።ስልጣን ለመያዝና ከያዘም በዃላ እንዳይወርድ ሲንከባከቡትና ሲረዱት የነበሩት አጋሮቹ ከጥቂት ጊዜ ወዲህ ጀርባቸውን እየሰጡት መጥተዋል።ይህ የሆነበት ምክንያት ስርዓቱ ን እንደፈረስ  ሊጠቀሙበት የሚችሉበት አስተማማኝ  ዕድል በህዝቡ ትግል እየተናደ በመምጣቱና ስርዓቱም ከድጡ ወደማጡ እየተዘፈቀ መመጣቱን በማጤን ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ እንዳይሆንባቸው በማሰብ ........... ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

  •  

 

 

 

 
 
 
 
 
 

Hits: 579

ህዝባችን የሚሻው መሰረታዊ ለውጥን እንጂ ቀጣይ ወታደራዊ አገዛዝንና ባዶ ተስፋን አይደለም


መጋቢት 7፣ 20009 (ማርች 16፣2017)
ሕወሀት/ ኢህአዴግ እንደተሽመደመደና መግዛት አንዳቃተው በተዘዋዋሪ አመነ።፤ይህ ሁኔታ ሰፊ የህዝብ መነሳሳትን ይቀስቅሳል ብሎ የፈራው ሕወሀት/ኢህአዴግ ከስድስት ወራት በፊት የጀመረውን ወታደራዊ አገዛዝ በመላ ኢትዮጵያ ይቀጥላል ሲል በጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርም ደሳለኝ በኩል በዛሬው እለት ለ”ፓርላማ” በቀረበው ሪፖርት አረጋግጧል። አስቂኝ የሆነው ይህ ንግግር፣ 82% የኢትዮጵያ ህዝብ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል ይፈልጋል ይላል። በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (65% ኢትዮጵያውያን) ስርአቱን ሙሉ በሙሉ እየተቃወሙት እንደሆነ እየታወቀ 82% ድጋፍ ከየት እንደሚመጣ የህወሀት/አህአዴግ በለስልጣኖች ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ እነርሱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሉት የህወሀት/ ኢህአዴግን አባላት ብቻ ከሆነ ሌላ ነገር ነው።

......

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

 

 
 

Hits: 998

የህዝብ እልቂት መሰረታዊ ምክንያት የመንግስት ግፍና ግድየሌሽነት ነው

መጋቢት 4፣ 2009 (ማርች 13፣ 2017)
በትላንትናው እለት በሀገራችን ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አባባ እጅግ ዘግናኝ እልቂት ተፈጽሟል። የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው ፣ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበት የነ በረው የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ ከስልሳ በላይ ወገኖቻችን በህይወት ተቀብረዋል። የስርአቱ ባለስልጣኖች ያመኑት 60 ግለሰቦች እንደሞቱ ይሁን እንጂ እውነ ተኛው ቁጥር ግን ከተባለው በላይ እጅግ ብዙ እንደሚሆን ይጠበቃል።

........ ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

 

 

Hits: 754