የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

ከድጡ ወደማጡ!!

 

ለህዝብ ደንታ የሌለውና የወዳጅ ምክር የማይቀበል መንግስት የመጨረሻ እጣ ፈንታው መወገድ ነው

ላለፉት ሃያስድስት ዓመታት በጉልበት ስልጣኑን ጨብጦ ያሻውን ሲያደርግ የኖረው የአምባገነን የዘረኞች ቡድን ከአሁን በዃላ እያጭበረበረና እየዋሸ፣እየገደለና እየዘረፈ የሚኖርበት ዘመኑ እየተመናመነ መምጣቱን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች ተከስተዋል።ስልጣን ለመያዝና ከያዘም በዃላ እንዳይወርድ ሲንከባከቡትና ሲረዱት የነበሩት አጋሮቹ ከጥቂት ጊዜ ወዲህ ጀርባቸውን እየሰጡት መጥተዋል።ይህ የሆነበት ምክንያት ስርዓቱ ን እንደፈረስ  ሊጠቀሙበት የሚችሉበት አስተማማኝ  ዕድል በህዝቡ ትግል እየተናደ በመምጣቱና ስርዓቱም ከድጡ ወደማጡ እየተዘፈቀ መመጣቱን በማጤን ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ እንዳይሆንባቸው በማሰብ ........... ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

  •  

 

 

 

 
 
 
 
 
 

Hits: 375

ህዝባችን የሚሻው መሰረታዊ ለውጥን እንጂ ቀጣይ ወታደራዊ አገዛዝንና ባዶ ተስፋን አይደለም


መጋቢት 7፣ 20009 (ማርች 16፣2017)
ሕወሀት/ ኢህአዴግ እንደተሽመደመደና መግዛት አንዳቃተው በተዘዋዋሪ አመነ።፤ይህ ሁኔታ ሰፊ የህዝብ መነሳሳትን ይቀስቅሳል ብሎ የፈራው ሕወሀት/ኢህአዴግ ከስድስት ወራት በፊት የጀመረውን ወታደራዊ አገዛዝ በመላ ኢትዮጵያ ይቀጥላል ሲል በጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርም ደሳለኝ በኩል በዛሬው እለት ለ”ፓርላማ” በቀረበው ሪፖርት አረጋግጧል። አስቂኝ የሆነው ይህ ንግግር፣ 82% የኢትዮጵያ ህዝብ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል ይፈልጋል ይላል። በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (65% ኢትዮጵያውያን) ስርአቱን ሙሉ በሙሉ እየተቃወሙት እንደሆነ እየታወቀ 82% ድጋፍ ከየት እንደሚመጣ የህወሀት/አህአዴግ በለስልጣኖች ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ እነርሱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሉት የህወሀት/ ኢህአዴግን አባላት ብቻ ከሆነ ሌላ ነገር ነው።

......

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

 

 
 

Hits: 717

የህዝብ እልቂት መሰረታዊ ምክንያት የመንግስት ግፍና ግድየሌሽነት ነው

መጋቢት 4፣ 2009 (ማርች 13፣ 2017)
በትላንትናው እለት በሀገራችን ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አባባ እጅግ ዘግናኝ እልቂት ተፈጽሟል። የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው ፣ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበት የነ በረው የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ ከስልሳ በላይ ወገኖቻችን በህይወት ተቀብረዋል። የስርአቱ ባለስልጣኖች ያመኑት 60 ግለሰቦች እንደሞቱ ይሁን እንጂ እውነ ተኛው ቁጥር ግን ከተባለው በላይ እጅግ ብዙ እንደሚሆን ይጠበቃል።

........ ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

 

 

Hits: 497

የችግሮቻችን መፍትሄ የሚገኘው ሁሉኑም ባለድርሻ ያሳተፈ ብሄራዊ መግባባትና እርቅን መሰረት ያደረገ ሀቀኛ ድርድር ሲካሄድ ነው።

 
  ባለድርሻ ያሳተፈ ብሄራዊ መግባባትና እርቅን መሰረት ያደረገ ሀቀኛ ድርድር ሲካሄድ ነው
 
 

........ ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

 

 

Hits: 689

ከጥር 5 እስከ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. (ጃንዋሪ 13-14) በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደው ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

 ከጥር 5 እስከ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. (ጃንዋሪ 13-14) በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደው
ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!
የአገር አድን የቀውጥ ጊዜ ግብረ ኃይል ተቋቋመ፤ ሁነኛ የአንድነት ኃይሎች አማራጭ በአጭር ጊዜ የማውጣት ሂደት ላይ ስምምነት ተደረሰ!አዘጋጅ የሆኑት ሶስት ድርጅትቶች (ሸንጎ፣ የሽግግር ምክር ቤትና የወጣቶች ንቅናቄ) ቀደም ሲል ሲያደርጉት የነበረውን ግንኙነት በማደስላለፉት 7 ወራት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ተከታታይ የሁለትዮሽና የወል ግንኙነቶችና ጥረቶችን በማድረግ ከቆዩ በኋላ፤ በአገራችን ጉዳይ ባለድርሻ ለሆኑ ለሁሉም የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ኦፊሽያል ጥሪ በማድረግ: እንደሚገኙ በደብዳቤ ካረጋገጡት 10 ድርጅቶች መካከል 9ኙበጥር 5 እና 6 ቀን 2009 ዓ.ም. (ጃንዋሪ 13 - 14 ቀን 20017) ተገኝተው የተሳካ ጉባዔ በዋሺንግተን ዲሲ ተከናውኗል አካሂደዋል፡፡
 
ይህ ጉባዔ የተከፈተው በስደት የሚገኘው ሕጋዊው ሲኖዶስ ተወካይና የዋሽንግተን ዲሲና የአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነሣሙኤል በሰጡት ቡራኬና ፀሎት ሲሆን፤ በተጨማሪም ጉባዔው ለአገርና ለሕዝብ የሚበጅ አንድ ውጤት ላይ እንዲደርስ ልባዊ ተማጽኖአቅርበዋል፡፡........To Read the full Document in PDF

 

 

Hits: 916