የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

ድንበራችንን ለማስከበር የተቃውሞ ድምጽወን ያስመዝግቡ

የካቲት 16፣ 2006 ( ፊበርዋሪ 22፣ 2014)

 

የሀገራችንን ዳር ድንበር ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በገዥው ህውሀት/ኢህአዴግ እና በሱዳን መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለውን ሴራ እንቃወማለን፡፡

ይህ ሴራ የሚካሄደው ህዝብን በማይወክል ጠባብ ቡድን በመሆኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ የሚፈጸመውን ማንኛውንም ውል እንደማንቀበል ካሁኑ እንዲታወቅልን ለተባበሩት መንግስታት፣ ለአፍሪካ ህብረት እና ለሌሎችም አለም አቀፍ ድርጅቶችና መሪወች የሚቀርብ የተቃውሞ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን።

እርሰወም ስመወን በማስፈር የዚሁ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አካል እንዲሆኑ በትህትና እንጠይቃለን። የናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበር  ሲደፈር ሁሉም የሚችለውን ማድረግ ሀገራዊ ግዴታው ነው።

http://www.ipetitions.com/petition/stop-secret-border-deal-between-ethiopia-and-Sudan

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር - to sign the petition click here