የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

አማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው

March 31, 2005

 

ህወሓት/ኢህአዴግ በህዛባችን ላይ የጫነው የጎሳ ፖለቲካ አስከፊ ገጽታው ላለፉት 22 ዓመታት በግልፅ እየሰፋ መጥታል።ያንዱንቋንቃ ተናጋሪ ከሌላው ጋር፣  የአንዱ አካባቢ ነዋሪ ከሌላው ጋር በአይነ ቁራኛና በአጥፊና ጠፊነት እንዲተያይ ተደርጓል።በዚህም የተነሳ የጎሳ ግጭት እጅግ ተስፋፍቷል። የህዝብ ህይወትና ንብረትም በሰፊው ጠፍቷል።የዜጎች የተረጋጋ ህይወት ተናግቷል።ይህ አጥፊ ፖሊሲም በአስቸኳይ  ካልተገታ ቀጣይና ምሰቅልቅል ቀውሰን እንደሚወልድ ግልጽ ሲሆን የዚህንም ቀውስ መጨረሻ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት እጅግ ይዘገንናል።