የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

የሽንጎው ከፍተኛ የአመራር አካል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

 

ነሃሴ ፯ ቀን ፳፻፭

Aug 13, 2013

የኢትዮጰያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ከፍተኛ የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ቅዳሜ ነሃሴ 4 ቀን፣ 2005 (Augest 10, 2013) በተሳካ ሁኔታ አካሄደ።

ይህ ስብሰባ የሽንጎው ሁለተኛ ጉባኤ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና የተለማቸውን የትግል አቅጣጫዎችበሀገር ውስጥና በውጭ  ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሰችሉ የተግባር  መመሪያዎችየሰጠ ሲሆን ይህንንም እውን ለማድረግ አስፈላጊ የሆ ኑ ኮሚቴዎችን መስርቷል፣የሰው ሀይልም መድቧል።

ምክር ቤቱ  በሀገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመመርመር ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ በተከታታይ ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ ህዝብን የማሸበር ተግባሩን በመቀጠል፣ በኢትዮጵያውያን ሰሊሞች ላይ በኢድ አል ፈጥርያካሄደውን ድብደባና ማንገላታትበታላቅ ሀዘን ተገንዝቧልድርጊቱንም በጥብቅአውግዟል።

በሰላማዊ መንገድ መሰረታዊ የእምት ነጻነት እንዲከበርና መንግስትም በሃማኖት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆምየታሰሩ የሀይማኖት መሪዎችም እንዲፈቱ የቀረበን ሰላማጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ስሊሙን ማህብረሰብ በጀምላበሽብርተኛና  አክራሪነት  የመወዘመቻ መቀጠሉእጅግ ሀላፊነት የጎደልውና አደገኛ እርምጃእንደሆነ በመገንዘብ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ከዚህ አይነት እኩይተግባሩ ተቆጥቦ ለሙስሊሙ ማህብረሰብ ያቄዎቸኳምላሽ እንዲሰጥ አሳሰቧል። ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር ያለውን የትግል አንድነት በድጋሜ ገልጿል።

ከዚህም ሌላ በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ ፣ በመድረክበሰማያዊ ፓርቲና በመኢአድ   አባላት ላይ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ እያካሄደ ያለውን እስራት  ወከባና ድብደባ ባሰቸኳይ እንዲያቆም፤ የህዝብንም መሰረታዊ መብቶችንና  የህግ የበላይነትእንዲያከብርጥብቅ አሳሰቧል።

ሽንጎው እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ  የህዝባችንን መብት ለማስከበር ቆራጥ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኙት ከነዚህ የተቃዋድርጅቶችና አባሎቻቸው ጋር ያለውን የትግል አንድነት በድጋሜ አረጋግጧል።

በመጨረሻምትግሉ ውጤታማ ለመሆንየተቃዋችን መተባበር  ግድ የሚል መሆኑንበመገንዘብ በኢትዮጵያ አንድነትና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ምስረታ ላይ ጽኑ እምነት ያላቸው ሁሉ አሁንም ሽንጎውን እንዲቀላቀሉ ቀጣይ ጥሪ አቅርቧል

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ