የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

የህወሓት/ኢህአዴግን አሸባሪ አገዛዝ በጋራ እንታገል

የካቲት 2፣ 2005   

Feb 9, 2013

 

ባለፉት ጥቂት ቀናት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በቁጥጥሩ ሥር የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎቶችን  በመጠቀም፣ በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎችን የሚወነጅል ሠፊ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ይህ “ጀሀዳዊ አራካት” በሚል ርዕስ በተደጋጋሚ በመሰራጨት ላይ ያለው  ፊልም፣  የሙስሊሙ ማህበረተሰብ የሀይማኖቱን አስተዳደር በተመለከተ ወክለው እንዲናገሩለት የመረጣቸው መሪዎቹ በእስር ላይ እያሉና ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት ተብየው እየታየ እያለ፣  እነዚህን በህዝብ የተመረጡ መሪዎች“እሰላማዊ መንግሥት ለመፍጠርና ሁከት ለማካሄድ የሚፈልጉ አሽባሪዎች”እንደሆኑበማሰመስል  በጥፋተኛነት የሚወነጅል ነው።