የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

ወገንተኛ ከሆነ የምርጫ ኮሚሽን ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ አይጠበቅም

ጥር ፫ ቀን ፳፻፯( January 11, 2007)

            ህወሓት/ኢህአዴግ  አሁንም  እንደገና  በሀገሪቱ  ምርጫ ሂደት ብቻውን ሮጦ  ብቻውን ለማሸነፍ እንዲችል አስከፊ አፈናውንና እመቃውን  አጠናክሮ ቀጥሏል።  ተፎካካሪ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከፖለቲካው በተለይም ከምርጫው ሂደት ተገፍትረው እንዲወጡ ለማድረግ ሳይታክት እየሰራ ነው። በሰሞኑም በአንድነት፣ በመኢአድና በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የምርጫ ቦርድ ተብየውን በመጠቀም የሚደረገው ማዋከብ ህወሓት/ኢህአዴግ በምርጫው ሂደት ውስጥ ብቻውን ከራሱ ጋር እንዲቀር ለማድረግ የሚያደርገው ጥረት አንድ ክፍል መሆኑ የማይታበል ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ( ሸንጎ) ይህ የወያኔ/ ኢህአዴግ ቀኝ እጅ የሆነው የምርጫ ቦርድ ተብየ እየወሰደ ያለውን አይን ያወጣ የአድሎ እርምጃ በጥብቅ ያወግዛል።....... ሙሉውን ያንብቡ